ዘኍል 32:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ተቈጥቶ ስለ ነበር፥ እነዚያ ያሳዘኑት ትውልዶች በሙሉ እስከሚያልቁ ድረስ ለአርባ ዓመት በምድረ በዳ እንዲንከራተቱ አደረጋቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ስለ ነደደ፣ በፊቱ ክፉ ነገር ያደረገው ያ ትውልድ በሙሉ እስኪያልቅ ድረስ አርባ ዓመት በምድረ በዳ እንዲንከራተቱ አደረጋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ በጌታም ፊት ክፉ ያደረገ ትውልድ ሁሉ እስኪጠፋ ድረስ አርባ ዓመት በምድረ በዳ ውስጥ አቅበዘበዛቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ በጠና ተቈጣ። በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ያደረገ ትውልድ ሁሉ እስኪጠፋ ድረስ አርባ ዓመት በምድረ በዳ ውስጥ አንከራተታቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ጸና፥ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ያደረገ ትውልድ ሁሉ እስኪጠፋ ድረስ አርባ ዓመት በምድረ በዳ ውስጥ አቅበዘበዛቸው። |
“እኔ ግን ለእናንተ ስል ቁመታቸው እንደ ሊባኖስ ዛፍ፥ ብርታታቸው እንደ ዋርካ ዛፍ የነበረውን አሞራውያንን ከነሥር መሠረታቸው ነቃቅዬ አጠፋሁላችሁ፤
“በእርግጥ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሠራችሁት ሥራ ሁሉ ብዙ በረከት ሰጥቶአችኋል፤ በዚህ በሰፊው በረሓ በሄዳችሁበት ሁሉ ተንከባክቦአችኋል፤ በእነዚህ በአርባ ዓመቶች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ስለ ነበረ ምንም የጐደለባችሁ ነገር አልነበረም።
ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ በጣም ተቈጣ፤ እንዲዘርፉአቸውም ለወራሪዎች አሳልፎ ሰጣቸው፤ በዙሪያቸው ያሉ ጠላቶቻቸውም እንዲበረቱባቸው አደረገ። ከዚያም በኋላ እስራኤላውያን ከጠላቶቻቸው ወረራ ራሳቸውን መከላከል ተሳናቸው።
ስለዚህ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ እጅግ ተቈጥቶ እንዲህ አለ፦ “ይህ ሕዝብ ከአባቶቹ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አፈረሰ፤ ትእዛዜን አልጠበቀም።