ዘኍል 31:49 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኛ አገልጋዮችህ፥ በእኛ ትእዛዝ ሥር የነበሩትን ወታደሮች ሁሉ ቈጥረናል፤ ከእነርሱ አንድም የጐደለ የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ አሉት፤ “እኛ አገልጋዮችህ በእጃችን ሥር ያሉትን ወታደሮች ቈጥረናል፤ አንድም የጐደለ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴንም እንዲህ አሉት፦ “እኛ ባርያዎችህ ወደ ጦርነት የወጡትን ከእጃችን በታች ያሉትን ቈጥረናል፥ ከእኛ አንድም ሰው አልጐደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ባሪያዎችህ ወደ ሰልፍ የወጡትን ከእጃችን በታች ያሉትን ቈጠሩ፤ ከእኛም አንድ አልጐደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴንም፦ እኛ ባሪያዎችህ ወደ ሰልፍ የወጡትን ከእጃችን በታች ያሉትን ቈጠርን፥ ከእኛም አንድ አልጐደለም። |
“የእስራኤልን ሕዝብ በምትቈጥርበት ጊዜ በሕዝብ ቈጠራው ወቅት መቅሠፍት እንዳይደርስባቸው እያንዳንዱ ሰው ለሕይወቱ ቤዛ የሚሆን ዋጋ ይክፈል።
ስለዚህ እያንዳንዳችን ያገኘነውን የወርቅ ጌጣጌጥ ማለትም የእግር አልቦውን፥ የእጅ አንባሩን፥ የጣት ቀለበቱን፥ የጆሮ ጒትቻውንና የአንገት ድሪውን ሁሉ ለኃጢአታችን ማስተስረያ ለእግዚአብሔር ቊርባን ይሆን ዘንድ ይዘን መጥተናል።”