ዘኍል 31:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ሙሴ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት መባውን ለእግዚአብሔር ልዩ ስጦታ በማድረግ ለአልዓዛር ሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው የእግዚአብሔር ድርሻ የሆነውን ግብር ለካህኑ አልዓዛር ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው ሙሴ ለጌታ የስጦታ ቁርባን የሆነውን ግብር ለካህኑ ለአልዓዛር ሰጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ሙሴ፦ ለእግዚአብሔር የለዩትን ግብር ለካህኑ ለአልዓዛር ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ሙሴ ለእግዚአብሔር ለማንሣት ቍርባን የሆነውን ግብር ለካህኑ ለአልዓዛር ሰጠው። |
“እስራኤላውያን ለእኔ የሚያቀርቡአቸውን ልዩ ስጦታዎች ሁሉ ለእናንተ፥ ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቻችሁ ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ቋሚ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ይህም ከእናንተና ከዘሮቻችሁ ሁሉ ጋር የምገባው የማይሻር የጨው ቃል ኪዳን ነው።”
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አሮንን እንዲህ አለው፦ “ለእኔ የሚቀርበውን የማይቃጠለውን ልዩ መባ ሁሉ ለአንተ የሰጠሁህ መሆኑን አስታውስ፤ እርሱ ለዘለዓለም ለአንተና ለዘሮችህ ሁሉ ድርሻ እንዲሆን ሰጥቻችኋለሁ፤
ለወታደሮቹ የተሰጡት ከወንድ ጋር ግንኙነት ያላደረጉ ሴቶች ዐሥራ ስድስት ሺህ ሲሆኑ፥ ከእነዚህም ሠላሳ ሁለቱ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለዩ ነበሩ።