“አሮንና ልጆቹ ከሚካኑበት አውራ በግ ተወስዶ ለመሥዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ። እርሱም ተመልሶ ለካህናቱ የሚመደብ ድርሻ ይሆናል።
ዘኍል 31:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእኔ ለእግዚአብሔር ልዩ ስጦታ በማድረግም ለካህኑ ለአልዓዛር ስጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህንም ግብር ከድርሻቸው ላይ ወስደህ የእግዚአብሔር ፈንታ በማድረግ ለካህኑ ለአልዓዛር ስጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከድርሻቸው ወስደህ ለጌታ እንደ ስጦታ ቁርባን አግርህ ለካህኑ ለአልዓዛር ትሰጠዋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከድርሻቸው እኩሌታ ወስደህ የእግዚአብሔርን ቀዳምያት ለካህኑ ለአልዓዛር ትሰጠዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከድርሻቸው ወስደህ ለእግዚአብሔር ለማንሣት ቍርባን ለካህኑ ለአልዓዛር ስጠው። |
“አሮንና ልጆቹ ከሚካኑበት አውራ በግ ተወስዶ ለመሥዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ። እርሱም ተመልሶ ለካህናቱ የሚመደብ ድርሻ ይሆናል።
“ለሌዋውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እግዚአብሔር ድርሻችሁ አድርጎ የሚሰጣችሁን ዐሥራት ከእስራኤላውያን በምትቀበሉበት ጊዜ፥ እናንተም በበኩላችሁ ከዚያው ከተቀበላችሁት የዐሥራት ዐሥራት በማውጣት ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጋችሁ አቅርቡ።
በዚህ ዐይነት እናንተም ከእስራኤላውያን ከምትቀበሉት ዐሥራት ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር የሚሆነውን ልዩ መባ ታቀርባላችሁ፤ ለእግዚአብሔር የምታመጡትን ይህን ልዩ መባ ለካህኑ አሮን ታስረክቡታላችሁ።
ለወታደሮቹ ከተመደበው ክፍል፥ ከአምስት መቶ እስረኞች አንዱን፥ እንዲሁም ከከብቱ፥ ከአህዮቹ፥ ከበጎቹና ከፍየሎቹ ከአምስት መቶው አንዱን እጅ ለእኔ ለእግዚአብሔር መባ አድርጋችሁ ለዩ፤
ለቀሩት የማኅበሩ አባላት ከተሰጠውም ክፍል ከኀምሳ እስረኞች አንዱን፥ በዚሁ መጠን ከከብቱ፥ ከአህዮቹ፥ ከበጎቹና ከፍየሎቹ ለይታችሁ ለተቀደሰው ድንኳን ኀላፊዎች ለሆኑት ሌዋውያን ስጡ።”
እናንተ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆቻችሁ፥ ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻችሁ፥ እንዲሁም ከእናንተ ጋር የርስት ክፍያ ከሌላቸው በከተሞቻችሁ ከሚኖሩ ከሌዋውያን ጋር በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ትደሰታላችሁ።