ዘኍል 30:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ቈየት ብሎ ስእለቱን የሚቃወም ከሆነ ለስእለቱ አለመፈጸም ኀላፊ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ነገሮቹ ከሰማ በኋላ እንዲቀሩ ካደረገ ግን ለፈጸመችው በደል በኀላፊነት የሚጠየቀው ራሱ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳሩ ግን ነገሩን ከሰማ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከንቱ ቢያደርገው በደልዋን ይሸከማል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰማው በኋላ ግን ቢከለክላት ኀጢአቱን ይሸከማል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰማው በኋላ ግን ከንቱ ቢያደርገው ኃጢአትዋን ይሸከማል። |
ባልዋ ስለ ጉዳዩ ሰምቶ ስእለትዋን እንዳትፈጽም ቢከለክላት ግን የመፈጸም ግዴታ የለባትም፤ ስእለትዋን ለመፈጸም ያልቻለችው ባልዋ ስለ ከለከላት በመሆኑ እግዚአብሔር ይቅርታ ያደርግላታል።
ነገር ግን ባልዋ ስለ ጉዳዩ በሰማበት ቀን ማግስት ምንም ተቃውሞ ያላቀረበ ከሆነ ስእለትዋንና በመሐላ የገባችውን ቃል ሁሉ መፈጸም ይኖርባታል፤ ስለ ጉዳዩ በሰማበት ቀን ተቃውሞ አለማቅረቡ ፈቃደኛ መሆኑን ያረጋግጣል።
ሳታገባ በአባትዋ ቤት የምትኖር ልጃገረድ ወይም ያገባች ሴት ስእለት ወይም የመሐላ ቃል በምትገባበት ጊዜ የአባት ወይም የባል ኀላፊነትንና መብትን በተመለከተ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው ደንብ ይህ ነው።
አባትዋ ስለ ጉዳዩ ሰምቶ ስእለትዋን እንዳትፈጽም የሚቃወማት ከሆነ ግን ስእለትዋን የመፈጸም ግዴታ አይኖርባትም፤ ስእለትዋን ለመፈጸም ያልቻለችው አባትዋ ስለ ከለከላት በመሆኑ እግዚአብሔር ይቅርታ ያደርግላታል።
ባልዋ ስለ ጉዳዩ ሰምቶ ከከለከላት ግን የመፈጸም ግዴታ የለባትም፤ ስእለትዋን ለመፈጸም ያልቻለችው ባልዋ ስለ ከለከላት በመሆኑ እግዚአብሔር ይቅርታ ያደርግላታል።