ዘኍል 28:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእያንዳንዱም ጠቦት ጋር ምርጥ በሆነ፥ በአንድ ሊትር የወይራ ዘይት የተለወሰ፥ አንድ ኪሎ ዱቄት የእህል ቊርባን ሆኖ ይቅረብ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም ጋራ ተወቅጦ በተጠለለ በሂን አንድ አራተኛ የወይራ ዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን አዘጋጁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኢንም መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት ለእህል ቁርባን ታቀርባለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእህልም ቍርባን የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ፥ ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ ዐሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት ታቀርባላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእህልም ቍርባን የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት ታቀርባለህ። |
ከእርሱም ጋር በየማለዳው ሳያስታጒል ሁለት ኪሎ ያኽል የእህል ቊርባንና ለምርጡ ዱቄት መለወሻ እንዲሆን አንድ ሊትር ዘይት ያዘጋጃል። ይህም የዘወትር ሥርዓት ይሆናል።
ይህም በፍጹም የሚቃጠለው የዘወትር መሥዋዕት ነው፤ የዚህ ዐይነቱ መሥዋዕት መዓዛው እኔን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የምግብ ቊርባን ሆኖ በመጀመሪያ የቀረበው በሲና ተራራ ላይ ነበር።
ያቀረባቸውም መባዎች እነዚህ ናቸው፦ በመቅደሱ ሚዛን መሠረት መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን አንድ ከብር የተሠራ ዝርግ ሳሕን፥ ከሰባ ሰቅል ብር የተሠራ አንድ ጐድጓዳ ሳሕን፥ ሁለቱም ለእህል ቊርባን በሚሆን ከዘይት ጋር በተቀላቀለ ደቃቅ ዱቄት የተሞሉ፥