አሮን የነአሶን እኅት የሆነችውን የዓሚናዳብን ልጅ ኤሊሼባን አገባ፤ እርስዋም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር የተባሉትን ወንዶች ልጆች ወለደችለት።
ዘኍል 26:61 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናዳብና አቢሁ ያልተቀደሰ እሳት ለእግዚአብሔር ከማቅረባቸው የተነሣ ተቀሥፈው ሞቱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ናዳብና አብዩድ ባልተፈቀደ እሳት ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ስላቀረቡ ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታም ፊት ያልተፈቀደውን እሳት ባቀረቡ ጊዜ ናዳብና አብዩድ ሞቱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሲና በረሃ በእግዚአብሔር ፊት ከሌላ እሳት ባቀረቡ ጊዜ ናዳብና አብዩድ ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔርም ፊት ሌላ እሳት ባቀረቡ ጊዜ ናዳብና አብዩድ ሞቱ። |
አሮን የነአሶን እኅት የሆነችውን የዓሚናዳብን ልጅ ኤሊሼባን አገባ፤ እርስዋም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር የተባሉትን ወንዶች ልጆች ወለደችለት።
ነገር ግን ከእነርሱ ውስጥ ናዳብና አቢሁ በሲና በረሓ በእግዚአብሔር ፊት ያልተቀደሰ እሳት ጭረው በማቅረባቸው ተቀሥፈው ሞቱ፤ እነርሱም ልጆች አልነበሩአቸውም፤ ስለዚህም አልዓዛርና ኢታማር ብቻ አባታቸው አሮን በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ በክህነት ያገለግሉ ነበር።