ከዚህ በኋላ የሳኦልንና የዮናታንን ዐፅም ወስደው በብንያም ጼላዕ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በሳኦል አባት በቂስ መቃብር ውስጥ በንጉሡ ትእዛዝ መሠረት ቀበሩ፤ ይህ ሁሉ ከተፈጸመም በኋላ ሕዝቡ ስለ አገራቸው ያቀረቡትን ጸሎት እግዚአብሔር ሰማ።
ዘኍል 25:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውየውና ሴቲቱ ወዳሉበት ድንኳን ገባ፤ ሁለቱንም በአንድነት በጦር ወግቶ ገደላቸው፤ በዚህም ዐይነት እስራኤላውያንን በማጥፋት ላይ የነበረው መቅሠፍት ቆመ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላዊውን ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ፤ ጦሩንም ወርውሮ እስራኤላዊውንና ሴቲቱን አጣምሮ ወጋቸው። ከዚያም በእስራኤላውያን ላይ የወረደው መቅሠፍት ተከለከለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያንንም የእስራኤልን ሰው ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ። እስራኤላዊውንም ሰውና ሴቲቱን ሁለቱንም ሆዳቸውን ወጋቸው። ከእስራኤልም ልጆች መቅሠፍቱ ተከለከለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያንም የእስራኤልን ሰው ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ። ሁለቱንም እስራኤላዊውን ሰውና ምድያማዊቱን ሴት ሆዳቸውን ወጋቸው፤ ከእስራኤልም ልጆች መቅሠፍቱ ተወገደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያንንም የእስራኤልን ሰው ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ። እስራኤላዊውንም ሰውና ሴቲቱን ሁለቱን ሆዳቸውን ወጋቸው። ከእስራኤልም ልጆች መቅሠፍቱ ተከለከለ። |
ከዚህ በኋላ የሳኦልንና የዮናታንን ዐፅም ወስደው በብንያም ጼላዕ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በሳኦል አባት በቂስ መቃብር ውስጥ በንጉሡ ትእዛዝ መሠረት ቀበሩ፤ ይህ ሁሉ ከተፈጸመም በኋላ ሕዝቡ ስለ አገራቸው ያቀረቡትን ጸሎት እግዚአብሔር ሰማ።
ለእግዚአብሔርም መሠዊያ ሠርቶ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት ሁሉ አቀረበ፤ እግዚአብሔርም የዳዊትን ጸሎት ሰማ፤ በእስራኤል ላይ የወረደውም የቸነፈር መቅሠፍት ከዚህ በኋላ ቆመ።
“የሰጠኋቸው ቃል ኪዳን የሕይወትና የሰላም ቃል ኪዳን ነው፤ እንዲሁም እኔን የማክበር ግዴታ አለባቸው፤ እነርሱም እኔን እየፈሩ ስሜን አክብረው ኖረዋል።
“የካህኑ የአሮን የልጅ ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ባደረገው ነገር ምክንያት በእስራኤል ሕዝብ ላይ ያለኝ ቊጣ በርዶአል፤ ፊንሐስ ከእኔ በቀር ለሌላ አምላክ የሚሰግዱትን መታገሥ አልፈለገም፤ በቊጣዬ እስራኤልን ያላጠፋሁትም እርሱ ስለ እኔ ባሳየው ቅናት ነው።
በእርሱም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ የሚታይ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት፤ እግዚአብሔርም ከቊጣው ተመለሰ፤ ስለዚህም ያ ቦታ የአኮር ሸለቆ ተብሎ ይጠራል።