ስለዚህ ከሳኦል ዘሮች ሰባት ወንዶችን ለእኛ አሳልፈህ ስጠን፤ እኛም እነርሱን እግዚአብሔር መርጦ ባነገሠው በንጉሥ ሳኦል ከተማ በጊብዓ በእግዚአብሔር ፊት እንሰቅላቸዋለን” ሲሉ መለሱ። ንጉሥ ዳዊትም “እነርሱን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው።
ዘኍል 25:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በእስራኤል ላይ የነደደው ቊጣዬ ይበርድ ዘንድ የእስራኤልን መሪዎች ሁሉ ወስደህ በጠራራ ፀሐይ በሕዝብ ፊት ግደላቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “አስፈሪው የእግዚአብሔር ቍጣ ከእስራኤል እንዲመለስ የሕዝቡን አለቆች ሁሉ ወስደህ ግደልና በጠራራ ፀሓይ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ስቀላቸው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የጌታ የቁጣው ጽናት ከእስራኤል እንዲመለስ የሕዝቡን አለቆች ሁሉ ወስደህ በፀሐይ ላይ በጌታ ፊት ስቀላቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስላፈረሱ የሕዝቡን አለቆች ሁሉ ወስደህ በፀሐይ ፊት ቅጣቸው። የእግዚአብሔርም ቍጣ ከእስራኤል ይርቃል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን፦ የእግዚአብሔር የቍጣው ጽናት ከእስራኤል እንዲመለስ የሕዝቡን አለቆች ሁሉ ወስደህ በፀሐዩ ፊት ወደ እግዚአብሔር ስቀላቸው አለው። |
ስለዚህ ከሳኦል ዘሮች ሰባት ወንዶችን ለእኛ አሳልፈህ ስጠን፤ እኛም እነርሱን እግዚአብሔር መርጦ ባነገሠው በንጉሥ ሳኦል ከተማ በጊብዓ በእግዚአብሔር ፊት እንሰቅላቸዋለን” ሲሉ መለሱ። ንጉሥ ዳዊትም “እነርሱን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው።
ዳዊት እነዚህን ሁሉ ለገባዖን ሰዎች አሳልፎ ሰጠ፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት በተራራው ላይ ሰቀሉአቸው፤ ሰባቱም በአንድነት ሞቱ፤ እነርሱም የተገደሉት በጸደይ ወራት ማለቂያና በገብስ መከር መጀመሪያ ላይ ነበር።
ከእስራኤላውያንም ሁሉ መካከል ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መረጠ፤ እነርሱንም የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የኀምሳ አለቆችና የዐሥር አለቆች አድርጎ በሕዝቡ ላይ ሾማቸው።
“የካህኑ የአሮን የልጅ ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ባደረገው ነገር ምክንያት በእስራኤል ሕዝብ ላይ ያለኝ ቊጣ በርዶአል፤ ፊንሐስ ከእኔ በቀር ለሌላ አምላክ የሚሰግዱትን መታገሥ አልፈለገም፤ በቊጣዬ እስራኤልን ያላጠፋሁትም እርሱ ስለ እኔ ባሳየው ቅናት ነው።
ይህንንም የምታደርጉት እናንተን በፔዖር በማታለል ግፍ ስለ ሠሩባችሁና በፔዖር በወረደው መቅሠፍት ምክንያት በተገደለችው በአለቃቸው ልጅ በኮዝቢ አማካይነት በፈጸሙት ሽንገላ ነው።”
እግዚአብሔር ከአስፈሪ ቊጣው ተመልሶ ምሕረት ያደርግልህ ዘንድ እንዲወድም ከተወሰነው ሀብት አንዳችም ለራስህ አታስቀር፤ ይህን ብታደርግ ለአባቶችህ በመሐላ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት ቊጥርህን ያበዛዋል።
በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር የተረገመ ስለ ሆነ አስከሬኑ በእንጨት ላይ ተሰቅሎ አይደር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በርስትነት የሚሰጥህን ምድር እንዳታረክስ አስከሬኑን በዚያኑ ዕለት ቅበረው።
በፔዖር ተራራ ላይ እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ ራሳችሁ በዐይናችሁ አይታችኋል፤ ይኸውም በዚያ ተራራ ላይ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ጣዖት የሚሰግዱትን ሁሉ ደምስሶአል፤
ስለዚህም እርሱ መላውን እስራኤልን፥ ሽማግሌዎችን፥ መሪዎችን፥ ዳኞችንና የጦር አዛዦችን በአንድነት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ እኔ በዕድሜ ሸምግያለሁ፤