በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ወደ በለዓም መጣና “እነዚህ ሰዎች ወደ አንተ የመጡት ይዘውህ ሊሄዱ ከሆነ ተነሥተህ አብረሃቸው ሂድ፤ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ አድርግ” አለው።
ዘኍል 23:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ተገናኘው፤ በለዓምም “ሰባቱን መሠዊያዎች ሠርቼ በእያንዳንዱ ላይ አንድ ኰርማና አንድ የበግ አውራ አቅርቤአለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ተገናኘው፤ በለዓምም፣ “እነሆ፤ ሰባት መሠዊያዎች አዘጋጅቻለሁ፤ በእያንዳንዱም ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ አቅርቤአለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ወደ በለዓም መጣ፤ እርሱም፦ “ሰባት መሠዊያዎች አዘጋጀሁ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈንና አንድ አውራ በግ አሳረግሁ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ለበለዓም ታየው፤ በለዓምም ለእግዚአብሔር፥ “እነሆ፥ ሰባት መሠዊያዎች አዘጋጀሁ፤ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈንና አንድ አውራ በግ አሳረግሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ከበለዓም ጋር ተገናኘ፤ እርሱም፦ ሰባት መሠዊያዎች አዘጋጀሁ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈንና አንድ አውራ በግ አሳረግሁ አለው። |
በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ወደ በለዓም መጣና “እነዚህ ሰዎች ወደ አንተ የመጡት ይዘውህ ሊሄዱ ከሆነ ተነሥተህ አብረሃቸው ሂድ፤ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ አድርግ” አለው።
ከዚህ በኋላ በለዓም ባላቅን “እግዚአብሔር ወደ እኔ መምጣቱን ወይም አለመምጣቱን ለማወቅ ወደዚያ ሄጄ እስክረዳ ድረስ እዚህ በሚቃጠል መሥዋዕትህ አጠገብ ቁም፤ እግዚአብሔር የሚገልጥልኝን ነገር ሁሉ እነግርሃለሁ” አለው፤ ከዚያም በኋላ ብቻውን ወደ አንድ ኮረብታ ወጣ።
‘እነዚህ በመጨረሻ መጥተው የሠሩት ለአንድ ሰዓት ብቻ ነው፤ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ በፀሐይ ሙቀት እየተቃጠልን በሥራ ስንደክም ከዋልነው ከእኛ ጋር እኩል አደረግሃቸው።’
እንግዲህ የምንመካበት ነገር ምን አለ? በምንም አንመካም! የማንመካበትስ ምክንያት ምንድን ነው? ሕግን ስለምንፈጽም ነውን? አይደለም፤ ነገር ግን በእምነት ነው።