ዘኍል 23:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ከዚህ በኋላ በለዓም ባላቅን “እግዚአብሔር ወደ እኔ መምጣቱን ወይም አለመምጣቱን ለማወቅ ወደዚያ ሄጄ እስክረዳ ድረስ እዚህ በሚቃጠል መሥዋዕትህ አጠገብ ቁም፤ እግዚአብሔር የሚገልጥልኝን ነገር ሁሉ እነግርሃለሁ” አለው፤ ከዚያም በኋላ ብቻውን ወደ አንድ ኮረብታ ወጣ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ከዚያም በለዓም ባላቅን፣ “እኔ ወደዚያ ስሄድ፣ አንተ እዚሁ መሥዋዕትህ አጠገብ ቈይ፤ ምናልባትም እግዚአብሔር ሊገናኘኝ ይመጣ ይሆናል፤ የሚገልጥልኝንም ሁሉ እነግርሃለሁ” አለው። ከዚያም በለዓም ወደ አንድ ገላጣ ኰረብታ ሄደ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 በለዓምም ባላቅን እንዲህ አለው፦ “በሚቃጠል መሥዋዕትህ ዘንድ ቆይ፥ እኔም እሄዳለሁ፤ ምናልባት ጌታ ሊያገኘኝ ይመጣል፤ እርሱም የሚገልጥልኝን እነግርሃለሁ።” ከዚያም እርሱ ወደ ኮረብታው ሄደ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 በለዓምም ባላቅን፥ “በመሥዋዕትህ ዘንድ ቈይ፤ እኔ እግዚአብሔር ቢገለጥልኝ፥ ቢገናኘኝም እሄዳለሁ፤ የሚገልጥልኝንም ቃል እነግርሃለሁ” አለው። ባላቅም በመሠዊያው ዘንድ ቆመ፤ በለዓም ግን እግዚአብሔርን ይጠይቅ ዘንድ አቅንቶ ሄደ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 በለዓምም ባላቅን፦ በመሥዋዕትህ ዘንድ ቆይ፥ እኔም እሄዳለሁ፤ ምናልባት እግዚአብሔር ሊገናኘኝ ይመጣል፤ እርሱም የሚገልጥልኝን እነግርሃለሁ አለው። ወደ ጉብታም ሄደ። Ver Capítulo |