ዘኍል 2:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን በየተመደቡበት ቡድን ሰንደቅ ዓላማና በየነገዳቸው ዐርማ ሥር ይሰፍራሉ፤ አሰፋፈራቸውም የመገናኛው ድንኳን በዙሪያው ሆኖ ፊታቸው ከድንኳኑ ትይዩ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እስራኤላውያን ከምስክሩ ድንኳን ትይዩ ዙሪያውን ጥቂት ራቅ ብለው እያንዳንዱ ሰው በየዐርማውና በየቤተ ሰቡ ምልክት ሥር ይስፈር።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የእስራኤል ልጆች እያንዳንዱ በየዓላማው በየአባቶቻቸው ቤቶች ምልክት ይስፈሩ፤ በመገናኛው ድንኳን ትይዩ በሁሉም አቅጣጫ ይስፈሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የእስራኤል ልጆች እያንዳንዱ በየሥርዐቱ፥ በየዓላማው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ አንጻር ይስፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ልጆች እያንዳንዱ በየዓላማው በየአባቶቻቸው ቤቶች ምልክት ይስፈሩ፤ በመገናኛው ድንኳን አፋዛዥ ዙሪያ ይስፈሩ። |
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህ በእስራኤላውያን መካከል ለዘለዓለም በምኖርበት ዙፋኔና የእግሬ ማሳረፊያ ነው፤ እስራኤላውያንና ንጉሦቻቸው ከእንግዲህ ወዲህ ጣዖት በማምለክና በንጉሦቻቸው ሞት ጊዜ በሚያደርጉአቸው ድርጊቶች ስሜን አያሰድቡም።
ያም ቀን ሲደርስ እረኛ በጎቹን ከአደጋ እንደሚያድን አምላካቸው እግዚአብሔር ሕዝቡን ያድናል። በዘውድ ላይ ያለ ጌጥ እንደሚያበራ፥ እነርሱም በእግዚአብሔር ምድር ያበራሉ።
በዚህ ፈንታ ሌዋውያንን በመገናኛው ድንኳንና በውስጡም ባሉት የመገልገያ ዕቃዎች ላይ ኀላፊዎች አድርገህ መድባቸው፤ እነርሱ ድንኳኑንና በውስጡ ያሉትን የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ይሸከማሉ፤ በድንኳኑም ውስጥ ያገለግላሉ፤ በዙሪያውም ይሰፍራሉ።
በመጨረሻም በዳን ነገድ ቡድን ሰንደቅ ዓላማ ሥር የሚገኙትና ለሁሉም ክፍሎች ደጀን የሚሆኑት በዓሚሻዳይ ልጅ በአሒዔዜር መሪነት የቡድን ተራቸውን ጠብቀው ተጓዙ።
እንግዲህ ከሁሉም በላይ ሕይወታችሁ የክርስቶስን ወንጌል የሚያስመሰግን ይሁን፤ ይህም እኔ መጥቼ ባያችሁም ወይም ከእናንተ ብርቅ በአንድ ዓላማ ጸንታችሁ መቆማችሁንና ወንጌልን በኅብረት ለማዳረስ መጋደላችሁን እሰማለሁ።
እንዲህ ያለ ሰው ራስ ከሆነው ከክርስቶስ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ አካልን በሙሉ በመገጣጠሚያና በጅማት አያይዞ የሚመግበው ራስ ነው። እግዚአብሔር ለአካል ሙሉ ዕድገት የሚሰጠውም በዚህ ዐይነት ነው።
ከዚህ በፊት ይህን ቦታ ስለማታውቁት የምትሄዱበትን መንገድ እነርሱ ያሳዩአችኋል፤ ነገር ግን ወደ ቃል ኪዳኑ ታቦት አትቅረቡ፤ በእናንተና በቃል ኪዳኑ ታቦት መካከል የሚኖረው ርቀት አንድ ኪሎ ሜትር ያኽል ይሁን።”