ዘኍል 19:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ንጹሕ የሆነ ሌላ ሰው የጊደርዋን ዐመድ ሰብስቦ በመውሰድ ከሰፈሩ ውጪ ንጹሕ በሆነ ቦታ ያስቀምጠዋል፤ እዚያም ለእስራኤላውያን ጉባኤ ርኲሰትን ለማንጻት የሚያገለግለውን ውሃ ለማዘጋጀት የሚጠቅም ይሆናል፤ ይህም ሥርዓት የሚፈጸመው ኃጢአትን ለማስወገድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ንጹሕ የሆነ ሰው የጊደሯን ዐመድ ዐፍሦ ከሰፈሩ ውጭ በመውሰድ በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ በሆነ ስፍራ ያኑረው፤ ይህም ርኩሰትን ለሚያነጻ ውሃ እንዲውል በእስራኤል ማኅበረ ሰብ የሚጠበቅ ይሆናል፤ ከኀጢአትም ለመንጻት ይጠቅማል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጹሕም ሰው የጊደሪቱን አመድ ይሰበስባል ከሰፈሩም ውጭ በንጹሕ ስፍራ ያኖረዋል፤ ርኩሰትንም የሚያነጻ ውኃ ተደርጎ ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ይጠበቃል፤ ከኃጢአት ለማንጻት የሚሆን ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጹሕም ሰው የጊደሪቱን አመድ ያከማቻል፤ ከሰፈሩም ውጭ በንጹሕ ስፍራ ያኖረዋል፤ ርኵሰት ለሚያነጻ ውኃ ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ይጠበቃል፤ ይነጹበታልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጹሕም ሰው የጊደሪቱን አመድ ያከማቻል ከሰፈሩም ውጭ በንጹሕ ስፍራ ያኖረዋል፤ ርኵሰትም ለሚያነጻ ውኃ ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ይጠበቃል፤ ከኃጢአት ለማንጻት የሚሆን ነው። |
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ጊዜ ለዳዊት ልጆችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከኃጢአታቸውና ከርኲሰታቸው የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።
ለማንጻት የተመደበው ውሃ በእርሱ ላይ ስላልፈሰሰ በድን ነክቶ ራሱን የማያነጻ፥ እንደ ረከሰ ይቈያል፤ እንዲህ ያለው ሰው ድንኳኑን ያረክሳል፤ ስለዚህም ከእስራኤል ሕዝብ ይለይ።
“ርኲሰቱንም ለማስወገድ፥ ለኃጢአት ማስተስረያ ከተቃጠለችው ጊደር ዐመድ ጥቂት ተወስዶ በማሰሮ ውስጥ ይከተት፤ ንጹሕ የምንጭ ውሃም ይጨመርበት፤
ቀጥሎም ንጹሕ የሆነ ሰው የሂሶጵ ቅርንጫፍ ወስዶ በውሃው ውስጥ እየነከረ በድንኳኑና በውስጡ በሚገኙት ዕቃዎች ሁሉ ላይ እንዲሁም በድንኳኑ ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ላይ ይርጨው፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ የሆነ ሰው ዐፅም ወይም ሬሳ ወይም መቃብር በነካው ሰው ላይ ውሃ ይርጭበት፤
በናዝራዊነትም ለማገልገል ራሱን እንደገና ለእግዚአብሔር የተለየ ያደርጋል፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰው ጠጒሩ ከመርከሱ የተነሣ ከዚያ በፊት በናዝራዊነት የነበረበት ክፍለ ጊዜ አይቈጠርለትም፤ ስለ በደልም ለሚከፈለው ዋጋ አንድ ዓመት የሞላው የበግ ጠቦት ያምጣ።
ለመንጻት ሥርዓት በተዘጋጀው ውሃ እርጫቸው፤ በሰውነታቸው ላይ ያለውን ጠጒር ሁሉ እንዲላጩና ልብሳቸውንም አጥበው ራሳቸውን እንዲያነጹ አድርግ፤
ንጹሕ የሆነ እና ወደ ሩቅ አገር ያልሄደ ማንኛውም ሰው የፋሲካን በዓል በወቅቱ ባያከብር ከሕዝቤ ይለይ፤ መባውን በተወሰነው ጊዜ ባለማቅረቡ፥ ስለ ኃጢአቱ ተገቢውን ቅጣት ይቀበላል።
እንግዲህ ወዳጆቼ ሆይ፥ ይህ ሁሉ ተስፋ የተሰጠው ለእኛ ስለ ሆነ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ከማናቸውም ነገር ራሳችንን እናንጻ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ቅድስናችን ፍጹም እንዲሆን እናድርግ።