አሮንና ልጆቹ ከምሽት እስከ ንጋት ይበራ ዘንድ የእግዚአብሔር መገኛ ከሆነው ፊት ከቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ካለው መጋረጃ ውጪ ያኑሩት፤ ይህም በእስራኤል ሕዝብና ወደፊትም በሚነሣው ትውልድ ዘንድ ቋሚ ሥርዓት ሆኖ ይኑር።
ዘኍል 18:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእንግዲህ ወዲህ ለመገናኛው ድንኳን እንክብካቤ የሚያደርጉትና ለእርሱም ሙሉ ኀላፊነት የሚኖራቸው ሌዋውያን ብቻ ናቸው፤ ይህም ለዘሮቻችሁ የሚተላለፍ የማይሻር ሕግ ሆኖ ይኖራል፤ ሌዋውያን ዘላቂነት ያለው ቋሚ ርስት በእስራኤል ምድር አይኖራቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመገናኛው ድንኳን የሚከናወነውን ሥራ የሚሠሩት ሌዋውያን ናቸው፤ በዚያም ለሚፈጸመው በደል ኀላፊነቱን ይሸከማሉ። ይህም ለሚመጡት ትውልዶች የዘላለም ሥርዐት ነው፤ ሌዋውያን በእስራኤላውያን መካከል ርስት አይሰጣቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌዋውያን ግን የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ያገለግላሉ፥ እነርሱም የራሳቸውን በደል ይሸከማሉ፤ ለልጅ ልጃችሁ ለዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል፤ በእስራኤልም ልጆች መካከል ርስት አይወርሱም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌዋውያን ግን የምስክሩን ድንኳን አገልግሎት ይሥሩ፤ እነርሱም ኀጢአታቸውን ይሸከማሉ፤ ለልጅ ልጃችሁም የዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል፤ በእስራኤልም ልጆች መካከል ርስት አይወርሱም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌዋውያን ግን የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ይሥሩ፥ እነርሱም ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ፤ ለልጅ ልጃችሁ ለዘላለም ሥርዓት ይሆናል፤ በእስራኤልም ልጆች መካከል ርስት አይወርሱም። |
አሮንና ልጆቹ ከምሽት እስከ ንጋት ይበራ ዘንድ የእግዚአብሔር መገኛ ከሆነው ፊት ከቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ካለው መጋረጃ ውጪ ያኑሩት፤ ይህም በእስራኤል ሕዝብና ወደፊትም በሚነሣው ትውልድ ዘንድ ቋሚ ሥርዓት ሆኖ ይኑር።
እግዚአብሔር አሮንን እንዲህ አለው፤ “በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በሚከናወነው አገልግሎት ስለሚፈጸመው በደል ሁሉ አንተና ልጆችህ፥ ሌዋውያንም ኀላፊነቱን ትሸከማላችሁ፤ በክህነት አገልግሎት ለሚፈጸመው በደል ግን ኀላፊነቱን የምትሸከሙት በተለይ አንተና ልጆችህ ብቻ ናችሁ።
እግዚአብሔር አሮንን እንዲህ አለው፦ “ለትውልድ የሚተላለፍ ምንም ዐይነት ርስት አትቀበልም፤ ከእስራኤልም ምድር የትኛውም ክፍል ለአንተ አይሆንም፤ እኔ እግዚአብሔር ራሴ ለአንተ ርስትህ ነኝ።”
ይህን ሕግ ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ መጠበቅ ይኖርባችኋል፤ ለማንጻት የሚያገለግለውን ውሃ በላዩ የሚረጨው ሰው ልብሱን ማጠብ ይኖርበታል፤ ውሃውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ያልነጻ ሆኖ ይቈያል፤
ዕድሜአቸው አንድ ወርና ከዚያም በላይ የሆነ የወንዶች ሌዋውያን ጠቅላላ ቊጥር ኻያ ሦስት ሺህ ሆነ፤ እነርሱም ከሌሎቹ እስራኤላውያን ተለይተው ተመዘገቡ፤ ይህም የሆነበት ምክንያት በእስራኤል ምድር ምንም ዐይነት የርስት ድርሻ ስላልተሰጣቸው ነበር።
የሌዊ ነገድ ከሌሎቹ ወንድሞቹ ጋር ርስት እንዲኖረው ያልተደረገበትም ምክንያት ይኸው ነው፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ አስቀድሞ እንደ ተናገረ ካህናት ሆነው የማገልገልን መብት በማግኘታቸው ራሱ እግዚአብሔር ለሌዋውያን ርስታቸው ነው።)
ሙሴ ለሌዊ ነገድ የርስት ድርሻ አልሰጠም፤ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር በመሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ ከሚቀርበው መባ የሚያገኙት ድርሻ እንደ ርስት ሆኖ ተመድቦላቸዋል።