ከዚህ በኋላ ሎጥ ሴቶች ልጆቹን ወዳጩአቸው ሰዎች ቤት ሄደና “ቶሎ ብላችሁ ከዚህ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህን ስፍራ ሊደመስሰው ነው” አላቸው፤ እነርሱ ግን የሚቀልድ መስሎአቸው ቸል አሉ።
ዘኍል 16:45 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከእነዚህ ሰዎች ርቃችሁ ቁሙ፤ እኔ እነርሱን በአንድ ጊዜ እደመስሳቸዋለሁ!” ሁለቱም በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በቅጽበት አጠፋቸዋለሁና ከዚህ ማኅበር ራቅ” እነርሱም በግንባራቸው ተደፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከዚህ ማኅበር መካከል ርቃችሁ ገለል በሉ፥ እኔም በአንድ ጊዜ አጠፋቸዋለሁ።” በግምባራቸውም ወድቀው ሰገዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከዚህ ማኅበር መካከል ፈቀቅ በሉ፥ እኔም በቅጽበት አጠፋቸዋለሁ።” በግንባራቸውም ወደቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህ ማኅበር መካከል ፈቀቅ በሉ፥ እኔም በቅጽበት አጠፋቸዋለሁ። በግምባራቸውም ወደቁ። |
ከዚህ በኋላ ሎጥ ሴቶች ልጆቹን ወዳጩአቸው ሰዎች ቤት ሄደና “ቶሎ ብላችሁ ከዚህ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህን ስፍራ ሊደመስሰው ነው” አላቸው፤ እነርሱ ግን የሚቀልድ መስሎአቸው ቸል አሉ።
ዳዊትም መልአኩ ኢየሩሳሌምን ለመደምሰስ ሰይፉን በእጁ እንደ ያዘ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ አየው፤ በዚህ ጊዜ ዳዊትና ማቅ ለብሰው የነበሩት የሕዝቡ አለቆች በሙሉ በግንባራቸው በመሬት ላይ ተደፉ።
ሕዝቡንም እንዲህ አለ፦ “ከእነዚህ ዐመፀኞች ሰዎች ድንኳኖች ርቃችሁ ቁሙ፤ የእነርሱ ንብረት የሆነውን ማናቸውንም ዕቃ አትንኩ፤ አለበለዚያ በእነርሱ ኃጢአት ምክንያት ሁላችሁም ከእነርሱ ጋር ተጠራርጋችሁ ትጠፋላችሁ።”
ሙሴና አሮን ከሕዝቡ ፈቅ ብለው ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሄዱ፤ በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው ሳሉም የእግዚአብሔር ክብር ተገለጠላቸው።
ከእነርሱ ጥቂት ራቅ ብሎ ሄደና፥ በመሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ፥ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “አባት ሆይ! የሚቻል ከሆነ ይህ የመከራ ጽዋ ከእኔ ወዲያ ይለፍ! ነገር ግን የአንተ ፈቃድ ይሁን እንጂ የእኔ ፈቃድ አይሁን።”