ንጉሥ ዖዝያ መንግሥቱን ባጠናከረ ጊዜ ዕብሪተኛ ሆነ፤ ይህም ዕብሪተኛነቱ ወደ ውድቀት አደረሰው፤ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን ለማጠን ወደ ቤተ መቅደስ በድፍረት በመግባቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ፤
ዘኍል 16:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እያንዳንዳቸው ጥናቸውን ይዘው የእሳት ፍምና ዕጣን በመጨመር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ከሙሴና ከአሮን ጋር ቆሙ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዱ ሰው ጥናውን በመያዝ ፍም አድርጎበት፣ ዕጣን ጨምሮበት ከሙሴና ከአሮን ጋራ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እያንዳንዳቸውም ጥናቸውን ወሰዱ፥ እሳትም አደረጉባቸው፥ ዕጣንም ጨመሩባቸው፥ ከሙሴና ከአሮንም ጋር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቆሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እያንዳንዱም ጥናውን ወሰደ፤ እሳትም አደረገበት፤ ዕጣንም ጨመረበት፤ ሙሴና አሮንም በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ቆሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እያንዳንዱም ጥናውን ወሰደ፥ እሳትም አደረገበት፥ ዕጣንም ጨመረበት፥ ከሙሴና ከአሮንም ጋር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቆመ። |
ንጉሥ ዖዝያ መንግሥቱን ባጠናከረ ጊዜ ዕብሪተኛ ሆነ፤ ይህም ዕብሪተኛነቱ ወደ ውድቀት አደረሰው፤ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን ለማጠን ወደ ቤተ መቅደስ በድፍረት በመግባቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ፤
ከመሠዊያው የሚቃጠል የእሳት ፍም በጥናው ሞልቶም ሁለት እፍኝ ጣፋጭ ሽታ ያለውን የተወቀጠ ደቃቅ ዕጣን በመውሰድ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ያግባ፤
እያንዳንዳችሁ ጥናችሁን ይዛችሁ ኑ፤ በውስጡም ዕጣን ጨምሩበት፤ ከሁለት መቶ ኀምሳ ጥናዎች ጋር ወደ እግዚአብሔር ፊት ዕጣናችሁን ታቀርባላችሁ፤ አንተና አሮንም ዕጣናችሁን ታቀርባላችሁ።”
ከዚያም በኋላ ቆሬ መላውን ማኅበር በአንድነት ሰበሰበ፤ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ መጥተው በሙሴና በአሮን ፊት ለፊት ቆሙ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ለመላው ማኅበር በድንገት ታየ።
“የአሮን ልጅ አልዓዛር ከነሐስ የተሠሩትን ጥናዎች ከተቃጠሉት ሰዎች ዘንድ እንዲወስድና ጥናዎቹ የተቀደሱ ስለ ሆኑ በውስጣቸው ያለውን ፍም ወደ ሌላ ስፍራ እንዲያፈስ ንገረው፤