ዘኍል 16:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ እናንተና ሌሎቹም ሌዋውያን ይህ ክብር እንዲኖራችሁ አድርጎአል፤ አሁን ደግሞ የካህናቱን ቦታ ለመያዝ ፈልጋችኋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተንና ከአንተም ጋራ ወገኖችህ የሆኑትን ሌዋውያንን ሁሉ ወደ ራሱ አቅርቧችኋል፤ እናንተ ግን የክህነቱንም ሥራ ደርባችሁ ለመያዝ ይኸው ትሯሯጣላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተን ከአንተም ጋር የሌዊን ልጆች ወንድሞችህን ሁሉ ወደ እርሱ እንድትቀርቡ ፈቅዶላችኋል፤ ታዲያ አሁን ደግሞ ክህነትንም ትፈልጋላችሁን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተን ከአንተም ጋር የሌዊን ልጆች ወንድሞችህን ሁሉ ወደ እርሱ አቅርቦአል፤ ካህናትም ትሆኑ ዘንድ ትፈልጋላችሁን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተን ከአንተም ጋር የሌዊን ልጆች ወንድሞችህን ሁሉ ወደ እርሱ አቅርቦአል፤ ክህነትንም ደግሞ ትፈልጋላችሁን? |
እግዚአብሔር አሮንን እንዲህ አለው፤ “በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በሚከናወነው አገልግሎት ስለሚፈጸመው በደል ሁሉ አንተና ልጆችህ፥ ሌዋውያንም ኀላፊነቱን ትሸከማላችሁ፤ በክህነት አገልግሎት ለሚፈጸመው በደል ግን ኀላፊነቱን የምትሸከሙት በተለይ አንተና ልጆችህ ብቻ ናችሁ።
ነገር ግን መሠዊያውንና ከመጋረጃው በስተውስጥ በኩል ያለውን ቅድስተ ቅዱሳኑን የሚመለከተውን የክህነት አገልግሎት የምትፈጽሙ አንተና ልጆችህ ብቻ ናችሁ፤ የክህነትን አገልግሎት ዕድል ፈንታ አድርጌ ስለ ሰጠኋችሁ ይህ ሁሉ ኀላፊነት የእናንተ ነው፤ ካህን ያልሆነ ማንኛውም ሰው ወደዚያ ቢቀርብ ይሞታል።”
በትሕትና ተሞልታችሁ ሌሎች ሰዎች ከእናንተ እንደሚሻሉ አድርጋችሁ ቊጠሩ እንጂ በራስ ወዳድነት ወይም “ያለ እኔ ማን አለ” በሚል ትምክሕት ምንም ነገር አታድርጉ።