ዘኍል 16:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሌዊ ነገድ የሆነው የቀዓት ጐሣ የይስዓር ልጅ ቆሬ፥ ከሮቤል ነገድ የሆኑት የኤልያብ ልጆች ዳታንና አቤሮን፥ የፋሌትም ልጅ ኦን ዐመፁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሌዊ ልጅ፣ የቀዓት ልጅ፣ የይስዓር ልጅ የሆነው ቆሬ፣ ከሮቤልም ነገድ የኤልያብ ልጆች ዳታንና አቤሮን እንዲሁም የፍሌት ልጅ ኦን በክፋት ተነሣሥተው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሌዊም ልጅ የቀዓት ልጅ የይስዓር ልጅ ቆሬ የኤልያብ ልጆች ዳታንንና አቤሮንን ከሮቤልም ልጆች የፋሌት ልጅ ኦንን ወሰዳቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሌዊም ልጅ የቀዓት ልጅ የይስዓር ልጅ ቆሬ ከኤልያብ ልጆች ከዳታንና ከአቤሮን፥ ከሮቤልም ልጅ ከፋሌት ልጅ ከአውናን ጋር ተናገረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሌዊም ልጅ የቀዓት ልጅ የይስዓር ልጅ ቆሬ ከሮቤልም ልጆች የኤልያብ ልጆች ዳታንና አቤሮን የፋሌትም ልጅ ኦን በሙሴ ላይ ተነሡ። |
ሌዊ ጌርሾን፥ ቀዓትና መራሪ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም በየስማቸው የሌዊ ነገድ አባቶች ናቸው፤ ሌዊ በሕይወት የኖረበት ዘመን 137 ዓመት ነበር።
“አባታችን አንድ እንኳ ወንድ ልጅ ሳይወልድ በምድረ በዳ ሞተ፤ እርሱ በእግዚአብሔር ላይ ካመፁት ከቆሬ ተከታዮች ጋር ተባባሪ አልነበረም፤ የሞተውም በራሱ ኃጢአት ምክንያት ነው፤
ከሮቤል ነገድ ወገን የኤልያብ ልጆች በሆኑት በዳታንና በአቤሮን ላይ ያደረገውን አስታውሱ፤ እስራኤላውያን ሁሉ በዐይናቸው እያዩ መሬት ተከፍታ እነርሱንና ቤተሰቦቻቸውን፥ ድንኳኖቻቸውንና ሕይወት ያለውና የእነርሱ የነበረውን ሁሉ ዋጠቻቸው።