ዘኍል 12:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ተቈጥቶ ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ቍጣ በላያቸው ነደደ፤ እርሱም ትቷቸው ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሱም ላይ የጌታ ቁጣ ነደደ፤ እርሱም ትቶአቸው ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ቍጣ በእነርሱ ላይ ወረደ፤ እርሱም ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ተቈጥቶባቸው ሄደ። |
እስራኤላውያን ስለ ደረሰባቸው ችግር ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ማጒረምረም ጀመሩ፤ እግዚአብሔርም የማጒረምረም ጩኸታቸውን ሰምቶ እጅግ በመቈጣት የሚባላ እሳት ላከባቸው፤ ያም እሳት ከሰፈሩ አንዱን ክፍል አወደመ።
ሕዝቡ ሁሉ በየድንኳኖቻቸው ደጃፍ ላይ በየቤተሰባቸው ቆመው ሲያለቅሱ ሙሴ ሰማቸው፤ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ተቈጥቶ ስለ ነበረ ሙሴ በጣም ተጨነቀ።