ዘኍል 1:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያንዳንዱ የራሱን ወገን ወክሎ በመምጣት በዐሥራ ሁለቱ የነገድ መሪዎች ርዳታ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው እነዚህ ናቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሙሴና በአሮን፣ እያንዳንዳቸውም ቤተ ሰባቸውን በወከሉት በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል አለቆች የተቈጠሩት ወንዶች እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነዚህ ተቈጥረው የነበሩ ናቸው፤ እነርሱን ሙሴና አሮን ከእስራኤል አለቆች፥ ዐሥራ ሁለት ሰዎች፥ እያንዳንዳቸው የአባቶቻቸውን ቤቶች ይወክሉ ከነበሩ ጋር በመሆን ቈጠሩአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴና አሮን ዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል አለቆች እነርሱን የቈጠሩበት ቍጥር ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተቈጠሩት፥ ሙሴና አሮን አሥራ ሁለቱም የእስራኤል አለቆች የቈጠሩአቸው፥ እነዚህ ናቸው፤ እያንዳንዱ የአባቶቹ ቤት አለቃ ነበረ። |