La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 1:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የብንያም ልጆች፥ በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸውና በየአባቶቻቸው ቤቶች እንደየስማቸው ቊጥር ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከብንያም ዝርያ፦ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“የብንያም ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለው፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የጋድ ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው- በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የብንያም ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥

Ver Capítulo



ዘኍል 1:36
10 Referencias Cruzadas  

እኛም ‘ሽማግሌ አባት አለን፤ በስተርጅና የወለደውም ታናሽ ወንድም አለን፤ የልጁ ወንድም ሞቶአል፤ ከእናቱ ልጆች የቀረው እርሱ ብቻ ስለ ሆነ አባቱ በጣም ይወደዋል’ ብለንህ ነበር፤


የብንያም ልጆች፦ ቤላዕ፥ ቤኬር፥ አሽቤል፥ ጌራ፥ ናዕማን፥ ኤሒ፥ ሮሽ፥ ሙፊም፥ ሑፊምና አረድ ናቸው።


“ብንያም እንደ ነጣቂ ተኲላ ነው፤ በማለዳ ያደነውን ራሱ ይበላል፤ በምሽት ያደነውን ግን ያካፍላል።”


ከብንያም ነገድ ለተመለመሉት ወታደሮች ዋና አዛዥ ኤሊያዳዕ ተብሎ የሚጠራ ጀግና ወታደር ነበር፤ በእርሱም ሥር ጋሻና ቀስት የያዙ ሁለት መቶ ሺህ ወታደሮች ነበሩ፤


ከምናሴ ነገድ የተቈጠሩት ሠላሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።


ከብንያም ነገድ የተቈጠሩት ሠላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።


ከዛብሎን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከዮሴፍ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከብንያም ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ ነበሩ።


በዚያን ቀን ብንያማውያን፥ ከየከተሞቻቸው ኻያ ስድስት ሺህ መሣሪያ የታጠቁ ሰዎችን አሰባሰቡ፤ ይህም ከጊብዓ ኗሪዎች ከተመረጡት ከሰባት መቶ ሰዎች ሌላ ነው።