ዘኍል 1:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጋድ ነገድ በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸውና በየቤተሰባቸው እንደየስማቸው ቊጥር ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ የተቈጠሩት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጋድ ዝርያ፦ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የጋድ ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለው፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳ ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደ እየስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጋድ ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥ |
እግዚአብሔር ስለ ዐሞን እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ወንዶች ልጆች የሉትምን? ወራሾች የሉትምን? ታዲያ ሚልኮም የተባለውን ጣዖት የሚያመልኩ ወገኖች የጋድን ነገድ አስለቅቀው በከተሞቹ የሰፈሩት ለምንድን ነው?