ዘኍል 1:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወታደር ሆነው ለማገልገል ችሎታ ያላቸው፥ ዕድሜአቸው ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆነ ወንዶች ከያዕቆብ ልጆች በኲር ከሆነው ከሮቤል ነገድ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእስራኤል የበኵር ልጅ ከሮቤል ዝርያ፦ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ሆኖ በሰራዊቱ ውስጥ ለማገልገል ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የእስራኤል በኩር የሮቤል ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ አንድ በአንድ፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን ወንድ ሁሉ፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል በኵር የሮቤል ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች እንደ እየስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው፥ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል በኵር የሮቤል ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው፥ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥ |
የያዕቆብ የበኲር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች ቀጥሎ የተመለከቱት ናቸው፤ (ሮቤል የአባቱን አልጋ ደፍሮ በማርከሱ የብኲርናውን መብት ስላጣ፥ ያ መብት ለዮሴፍ ተሰጥቶ ነበር፤