ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና ሓሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፥ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳኑን አደሰ፤ ስለዚህም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ፤ ሕዝቡም በቃል ኪዳኑ ተባበረ።
ነህምያ 9:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እኛ የጽሑፍ ስምምነት ለማድረግ ወሰንን፤ በስምምነቱም ጽሑፍ ላይ መሪዎቻችን፥ ሌዋውያኖቻችንና ካህናቶቻችን ማኅተማቸውን አኖሩበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከዚህ ሁሉ የተነሣም ጽሑፍ ላይ በማስፈር ግዴታ የምንገባበትን የውል ስምምነት እናደርጋለን፤ መሪዎቻችን፣ ሌዋውያናችንና ካህናታችንም ማኅተሞቻቸውን ያኖሩበታል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም ሁሉ የታመነውን ቃል ኪዳን አድርገን እንጽፋለን፤ አለቆቻችንም፥ ሌዋውያኖቻችንም፥ ካህናቶቻችንም ያትሙበታል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም ሁሉ የታመነውን ቃል ኪዳን አድርገን እንጽፋለን፥ አለቆቻችንም ሌዋውያኖቻችንም ካህናቶቻችንም ያትሙበታል። |
ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና ሓሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፥ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳኑን አደሰ፤ ስለዚህም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ፤ ሕዝቡም በቃል ኪዳኑ ተባበረ።
“ከእንግዲህ ወዲህ የእግዚአብሔር ቊጣ ከእኛ እንዲርቅ እነሆ እኔ አሁን ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት ወስኛለሁ፤
ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና ሐሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፥ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳኑን አደሰ፤ ስለዚህም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ።
አሁን እንግዲህ እነዚህን ባዕዳን ሴቶች ከነልጆቻቸው ማሰናበት እንደሚገባን ለአምላካችን ቃል እንግባ፤ አንተ ጌታዬና የአምላካችንን ትእዛዝ የሚያከብሩ ሌሎችም የምትሰጡንን ምክር ሁሉ እንፈጽማለን፤ የእግዚአብሔር ሕግ የሚያዘውን ሁሉ እናደርጋለን፤
እነዚህ ሁሉ ወንድሞቻቸው ከሆኑት መሪዎቻቸው ጋር ተባብረው በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴ አማካይነት ለተሰጡት ለጌታችን ለእግዚአብሔር ትእዛዞች፥ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ሁሉ ታዛዦች እንደሚሆኑ በእርግማንና በመሐላ ቃል ገቡ።
“አንዱ ‘እኔ የእግዚአብሔር ነኝ’ ይላል፤ ሌላው በያዕቆብ ስም ይጠራል፤ ሌላው ደግሞ ‘የእግዚአብሔር ሰው ነኝ’ ብሎ በእጁ ላይ ይነቅሳል፤ እስራኤል በሚለውም ስም ይጠራል።”