Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ነህምያ 10:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ያተሙትም የሐካልያ ልጅ የሆነው አገረ ገዢው ነህምያ፥ ሴዴቅያስ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ያተሙትም እነዚህ ናቸው፦ የሐካልያ ልጅ አገረ ገዥው ነህምያ። ሴዴቅያስ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በዚህም ሁሉ የታመነውን ቃል ኪዳን አድርገን እንጽፋለን፤ መሪዎቻችን፥ ሌዋውያኖቻችንና ካህናቶቻችን ያትሙበታል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ያተ​ሙ​ትም እነ​ዚህ ናቸው፤ የሐ​ካ​ልያ ልጅ ሐቴ​ር​ሰታ ነህ​ምያ፥ ሴዴ​ቅ​ያስ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ያተሙትም እነዚህ ናቸው፥ የሐካልያ ልጅ ሐቴርሰታ ነህምያ፥

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 10:1
11 Referencias Cruzadas  

ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና ሓሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፥ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳኑን አደሰ፤ ስለዚህም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ፤ ሕዝቡም በቃል ኪዳኑ ተባበረ።


አሁን እንግዲህ እነዚህን ባዕዳን ሴቶች ከነልጆቻቸው ማሰናበት እንደሚገባን ለአምላካችን ቃል እንግባ፤ አንተ ጌታዬና የአምላካችንን ትእዛዝ የሚያከብሩ ሌሎችም የምትሰጡንን ምክር ሁሉ እንፈጽማለን፤ የእግዚአብሔር ሕግ የሚያዘውን ሁሉ እናደርጋለን፤


በኡሪምና በቱሚም የእግዚአብሔርን ፈቃድ መጠየቅ የሚችል ካህን እስከሚነሣም ድረስ እነርሱ የተቀደሰውን ምግብ መብላት እንደማይችሉ ገዢው አዘዛቸው።


የሐካልያ ልጅ ነህምያ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ አርጤክስስ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት በሆነ በሃያኛው ዓመት ኪስሌው ተብሎ በሚጠራው ወር እኔ ነህምያ ዋና ከተማ በሆነችው በሱሳ ውስጥ ነበርኩ።


ከካህናት ወገን፦ ሠራያ፥ ዐዛርያ፥ ኤርምያስ፥ ፓሽሑር፥ አማርያ፥ ማልኪያ፥ ሐጡሽ፥ ሸባንያ፥ ማሉክ፥ ሐሪም፥ መሬሞት፥ አብድዩ፥ ዳንኤል፥ ጊነቶን፥ ባሩክ፥ መሹላም፥ አቢያ፥ ሚያሚን፥ መዓዝያ፥ ቢልጋይና ሸማዕያ።


በአካባቢአችን ላሉት አሕዛብ ሴቶች ልጆቻችንን በጋብቻ እንደማንሰጥና ወይም የእነርሱን ሴቶች ልጆች ለወንዶች ልጆቻችን በጋብቻ እንደማንወስድ ቃል እንገባለን።


ስለዚህም የይሁዳ ገዥ በኡሪምና በቱሚም የሚያገለግል ካህን እስከሚነሣበት ጊዜ ድረስ ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ ከሚቀርበው ቊርባን መመገብ የማይችሉ መሆናቸውን ነገራቸው።


አንዳንድ የቤተሰብ መሪዎችም ቤተ መቅደሱን እንደገና ለመሥራት የሚረዳ አስተዋጽዖ አድርገዋል፤ ከእነርሱም መካከል፥ አገረ ገዢው፦ 8 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 50 ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ 530 የካህናት ልብሶችን ሰጠ። የጐሣ አለቆችም፦ 168 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 1250 ኪሎ የሚመዝን ብር ሰጡ፤ የቀሩት ሰዎችም፦ 168 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 1100 ኪሎ የሚመዝን ብርና 67 የካህናት ልብሶችን ሰጥተዋል።


የሕጉን ቃል በሰሙ ጊዜ ሰዎቹ ስላለቀሱ፥ አገረ ገዢው ነህምያ፥ ካህኑና የሕግ ምሁሩ ዕዝራ፥ ሕዝቡን ያስተምሩ የነበሩት ሌዋውያን “ይህ ቀን ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ቀን ስለ ሆነ፥ አትዘኑ፤ አታልቅሱም” አሉአቸው።


ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እኛ የጽሑፍ ስምምነት ለማድረግ ወሰንን፤ በስምምነቱም ጽሑፍ ላይ መሪዎቻችን፥ ሌዋውያኖቻችንና ካህናቶቻችን ማኅተማቸውን አኖሩበት።


ሙሴም የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ ጻፈ፤ በማግስቱም ጠዋት በማለዳ በተራራው ሥር መሠዊያ ሠራ፤ ለእያንዳንዱም የእስራኤል ነገድ አንድ የድንጋይ ዐምድ አኖረ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos