ነህምያ 6:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ዐይነት ሥራውን እንድናቆም ለማድረግ ያስፈራሩን ነበር፤ ስለዚህም “እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! እባክህ አበርታኝ!” ስል ጸለይኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉም፣ “እጃቸው መሥራት እስኪሳነው ድረስ ይዝላል፤ ሥራውም ሳይጠናቀቅ ይቀራል” ብለው በማሰብ ሊያስፈራሩን ሞከሩ። እኔ ግን፣ “አሁንም እጄን አበርታ” ስል ጸለይሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉም እንዲህ እያሉ አስፈራሩን፦ “ከሥራው እጃቸውን ያላላሉ፥ አይሠራምም” አሁንም እጄን አበርታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ሁሉ ሥራው እንዳይፈጸም፥ “እጃቸው ይደክማል” ብለው አስፈራሩን፤ ስለዚህም እጆችን አበረታሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ሁሉ ሥራው እንዳይፈጸም፦ እጃቸው ይደክማል ብለው ያስፈራሩን ዘንድ ወደዱ፥ አሁንም፥ አምላክ ሆይ፥ እጄን አበርታ። |
የአሦር ባለሥልጣኖች ይህን የዛቻ ቃል በዕብራይስጥ ቋንቋ በቅጽሮቹ ላይ ለነበሩት ለኢየሩሳሌም ሰዎች ከፍ ባለ ድምፅ ያሰሙ ነበር፤ ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት ሕዝቡን አስፈራርተው ተስፋ በማስቈረጥ ከተማይቱን በቀላል ለመያዝ ዐቅደው ነው።
ጐረቤቶቻቸውም ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ዕቃዎችን፥ ቈሳቊሶችንና ከብቶችን፥ ሌሎችንም ጠቃሚ የሆኑ ስጦታዎችና በቤተ መቅደስ መባ ሆኖ የሚቀርብ ሌላም ነገር በመለገሥ ረዱአቸው።
እኔም “አምላክ ሆይ፥ ጦቢያና ሰንባላጥ ያደረጉትን ሁሉ ተመልከት፤ ፍረድባቸውም፤ ኖዓድያ የተባለችው ሴት ነቢይትና ሌሎቹም ነቢያት እኔን ለማስፈራራት ያደረጉትን ሁሉ አስብ” በማለት ጸለይኩ።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከመቅደሱ በሚገለጥበት ጊዜ እጅግ ያስፈራል፤ እርሱ ለሕዝቡ ብርታትንና ኀይልን ይሰጣል። እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።
ከዚህ በኋላ መኳንንቱ ወደ ንጉሡ ሄደው እንዲህ አሉት፦ “ይህ ሰው ሞት ይገባዋል፤ በእንደዚህ ያለ አነጋገር እየተናገረ በከተማይቱ የቀሩት ወታደሮች ወኔ እንዳይኖራቸው አድርጎአል፤ በከተማይቱ ሰው ሁሉ ላይ የሚያደርገው ይኸው ነው፤ ሕዝቡን ለመጒዳት እንጂ ለመርዳት የሚፈልግ ሰው አይደለም።”
በዚህም ዐይነት የባቢሎንን ንጉሥ ኀይል በማጠንከር የእኔን ሰይፍ በእጁ አስይዘዋለሁ። የግብጽን ንጉሥ ኀይል ግን እሰብራለሁ፤ እርሱም ለሞት የሚያደርስ ቊስል እንደ ደረሰበት ሰው በጠላቱ ፊት ይቃትታል።
ነገር ግን እርሱ “የእኔ ኀይል ፍጹም ሆኖ የሚገለጠው በአንተ ደካማነት ስለ ሆነ ጸጋዬ ይበቃሃል” አለኝ፤ ስለዚህ የክርስቶስ ኀይል በእኔ ላይ እንዲሆን ከምን ጊዜውም ይልቅ በደካማነቴ ደስ እያለኝ ልመካ እወዳለሁ።
ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ በክርስቶስ ወደ ዘለዓለም ክብር የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ እርሱ ራሱ ከተቀበላችሁት መከራ ያድናችኋል፤ ይደግፋችኋል፤ ያጸናችኋል፤ ይመሠርታችኋልም።
ሰዎቹ ሁሉ በሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸው መማረክ ምክንያት ተማርረው ስለ ነበረ በድንጋይ ሊወግሩት በመነጋገራቸው ዳዊት በታላቅ አደጋ ላይ ነበር። እርሱ ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አጽናና፤