ነህምያ 3:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ቅጽር የሠሩ ካህናት ስም ዝርዝር ይህ ነው፦ በኢየሩሳሌም ዙሪያ የነበሩት ካህናት ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱም ቀጥሎ ያለውን ክፍል ከአካባቢው የመጡት ካህናት መልሰው ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱ በኋላ የአካባቢው ሰዎች ካህናቱ አደሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም በኋላ የአካባቢው ሰዎች ካህናቱ ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም በኋላ የቈላው ሰዎች ካህናቱ አደሱ። |
ከእነርሱም ቀጥሎ ብንያምና ሐሹብ በመኖሪያ ቤቶቻቸው ፊት ለፊት ያለውን ክፍል ሠሩ። የዐናኒያ የልጅ ልጅ የሆነውም የመዕሤያ ልጅ ዐዛርያ በራሱ መኖሪያ ቤት አጠገብ ያለውን ክፍል ሠራ።
ከዚህም የተነሣ ሰንባላጥና ጌሼም በተለይ ኦኖ ተብሎ በሚጠራው ሜዳ ከሚገኙት መንደሮች በአንዲቱ እንድንገናኛቸው መልእክት ላኩብኝ፤ ይህም እኔን ለመጒዳት በተንኰል የተዶለተ ዘዴ ነበር።