ነህምያ 3:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሓሪም ልጅ ማልኪያና የፓሐትሞአብ ልጅ ሐሹብ ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍልና “የእቶን ግንብ” ተብሎ የሚጠራውን ግንብ ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የካሪም ልጅ መልክያና የፈሐት ሞዓብ ልጅ አሱብ ሌላውን ክፍልና የእቶን ግንብ ተብሎ የሚጠራውን መልሰው ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሐሪም ልጅ ማልኪያና የፓሐት ሞዓብ ልጅ ሐሹብ ሌላውን ክፍልና “የእቶን ግንብ” አደሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካሪም ልጅ መልክያ፥ የፈሐት ሞዓብ ልጅም አሱብ ሌላውን ክፍልና የእቶኑን ግንብ ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካሪም ልጅ መልክያ፥ የፈሐት ሞዓብ ልጅም አሱብ ሌላውን ክፍልና የእቶኑን ግንብ አደሱ። |
ከሕዝቡ መሪዎች ወገን፦ ፓርዖሽ፥ ፓሐትሞአብ፥ ዔላም፥ ዛቱ፥ ባኒ፥ ቡኒ፥ ዓዝጋድ፥ ቤባይ፥ አዶኒያ፥ ቢግዋይ፥ ዓዲን፥ አጤር፥ ሕዝቅያስ፥ ዓዙር፥ ሆዲያ፥ ሐሹም፥ ቤጻይ፥ ሐሪፍ፥ ዐናቶት፥ ኔባይ፥ ማግፒዓሽ፥ መሹላም፥ ሔዚር፥ መሼዛብኤል፥ ጻዶቅ፥ ያዱዐ፥ ፐላጥያ፥ ሐናን፥ ዓናያ፥ ሆሴዕ፥ ሐናንያ፥ ሐሹብ፥ ሀሎሔሽ፥ ፒልሐ፥ ሾቤቅ፥ ረሑም፥ ሐሻብና፥ ማዕሤያ፥ አኪያ፥ ሐናን፥ ዓናን፥ ማሉክ፥ ሐሪምና በዓና።
ሌላው የመዘምራን ቡድን ሰልፍ የቅጽሩን ግንብ ጫፍ በመከተል ወደ ግራ በኩል አለፈ፤ እኔም ከሕዝቡ እኩሌታ ጋር ይህንኑ የቡድን ሰልፍ እከተል ነበር፤ የእቶኑንም ግንብ አልፈን ወደ ሰፊው ቅጽር ግንብ ደረስን።