ይህ በዚህ እንዳለ የአሦር ንጉሠ ነገሥት እንደገና የተጠናከረ ታላቅ ሠራዊት ከላኪሽ ተንቀሳቅሶ ወደ ኢየሩሳሌም በመዝመት በሕዝቅያስ ላይ አደጋ እንዲጥልበት አዘዘ፤ ያም ሠራዊት ከፍተኛ ሥልጣን ባላቸው ሦስት የጦር አዛዦቹ የሚመራ ነበር፤ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ደረሱ ከላይኛው ኲሬ ውሃ በሚተላለፍበት ቦይ አጠገብ ወደ ልብስ አጣቢዎች መስክ የሚወስደውን መንገድ ያዙ፤
ነህምያ 2:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ከከተማይቱ በስተ ምሥራቅ በኩል በሰሜን ወደሚገኘው “የውሃ ምንጭ ቅጽር በር” ተብሎ በሚጠራው ስፍራና ወደ ንጉሡ ኲሬ ሄድኩ፤ ነገር ግን ተቀምጬበት የነበረው እንስሳ የፍርስራሹን ክምር ለማለፍ የሚያስችለው መንገድ ማግኘት አልቻለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ወደ ውሃ ምንጭ በርና ወደ ንጉሡ ኵሬ ሄድሁ፤ ይሁን እንጂ የተቀመጥሁበትን እንስሳ ማሳለፍ የሚያስችል በቂ ቦታ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ “የምንጭ በር” እና ወደ ንጉሡ መዋኛ አለፍኩ፤ ሆኖም ተቀምጬበት የነበረውን እንስሳ አያሳልፈውም ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ምንጩም በርና ወደ ንጉሡም መዋኛ አለፍሁ፤ ተቀምጬበት የነበረው እንስሳም የሚያልፍበት ስፍራ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ምንጩም በርና ወደ ንጉሡ መዋኛ አለፍሁ፤ ተቀምጬበትም የነበረው እንስሳ የሚያልፍበት ስፍራ አልነበረም። |
ይህ በዚህ እንዳለ የአሦር ንጉሠ ነገሥት እንደገና የተጠናከረ ታላቅ ሠራዊት ከላኪሽ ተንቀሳቅሶ ወደ ኢየሩሳሌም በመዝመት በሕዝቅያስ ላይ አደጋ እንዲጥልበት አዘዘ፤ ያም ሠራዊት ከፍተኛ ሥልጣን ባላቸው ሦስት የጦር አዛዦቹ የሚመራ ነበር፤ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ደረሱ ከላይኛው ኲሬ ውሃ በሚተላለፍበት ቦይ አጠገብ ወደ ልብስ አጣቢዎች መስክ የሚወስደውን መንገድ ያዙ፤
ንጉሥ ሕዝቅያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ የጀግንነት ሥራው ጭምር፥ እንዲሁም የውሃ ማጠራቀሚያ ግድብ እንዴት እንደ ሠራና ወደ ከተማይቱ ውሃ ለማምጣት ያስቈፈረው የመሬት ውስጥ ቦይ አሠራር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።
በላይ በኩል ያለውን የግዮንን ምንጭ መውጫ ገድቦ ውሃውን ወደ ምዕራብ፥ ወደ ዳዊት ከተማ፥ በቦይ እንዲወርድ ያደረገ ራሱ ሕዝቅያስ ነው፤ ይህ ሕዝቅያስ ሊሠራ ባቀደው ነገር ሁሉ የተሳካለት ሰው ነበር፤
ወደ ውሃው ምንጭ በር እንደ ደረሱም ወደ ዳዊት ከተማ አቅንተው በቅጽሩ ላይ ያሉትን ደረጃዎች በመውጣትና የዳዊትን ቤተ መንግሥት በማለፍ ከከተማይቱ በስተምሥራቅ ወደሚገኘው ወደ ውሃ ቅጽር በር ተመለሱ።
የምጽጳ ወረዳ ገዢ የሆነው የኮልሖዜ ልጅ ሻሉም የምንጩን ቅጽር በር እንደገና ሠራ፤ ክዳን ከሠራለትም በኋላ መዝጊያዎችን አቆመ፤ ለበሮቹም ቊልፎችንና መወርወሪያዎችን አበጀ፤ በሼላሕ ኩሬ ቅጥር በኩል ከቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ ጀምሮ ከዳዊት ከተማ ወደታች እስከሚያወርደው ደረጃ ድረስ ያለውን ክፍል እንደገና ሠራ።
የቤትጹር አውራጃ እኩሌታ ገዢ የነበረው የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ እስከ ዳዊት መቃብር (ከዳዊት መቃብር ትይዩ ጀምሮ)፥ እስከ ኩሬ፤ እስከ ጀግኖች ሰፈር ድረስ ያለውን ክፍል ሠራ።