ነህምያ 12:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም37 ወደ ውሃው ምንጭ በር እንደ ደረሱም ወደ ዳዊት ከተማ አቅንተው በቅጽሩ ላይ ያሉትን ደረጃዎች በመውጣትና የዳዊትን ቤተ መንግሥት በማለፍ ከከተማይቱ በስተምሥራቅ ወደሚገኘው ወደ ውሃ ቅጽር በር ተመለሱ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም37 ከምንጭ በር ተነሥተው በቀጥታ ወደ ዳዊት ከተማ ደረጃዎች ወጡ፤ ከዚያም በቅጥሩ መውጫ በኩል አድርገው ከዳዊት ቤት በላይ በስተምሥራቅ ወደሚገኘው ወደ ውሃ በር ሄዱ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)37 “በምንጭ በር” አቅንተው ሄዱ፤ በዳዊትም ከተማ ደረጃ፥ በቅጥሩም መውጫ፥ ከዳዊትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በምሥራቅ በኩል ሄዱ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)37 በምንጭም በር አቅንተው ሄዱ፤ በዳዊትም ከተማ ደረጃ፥ በቅጥሩም መውጫ፥ ከዳዊትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በምሥራቅ በኩል ሄዱ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)37 በምንጭም በር አቅንተው ሄዱ፥ በዳዊትም ከተማ ደረጃ፥ በቅጥሩም መውጫ፥ ከዳዊትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በምሥራቅ በኩል ሄዱ። Ver Capítulo |