Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ነህምያ 3:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የቤትጹር አውራጃ እኩሌታ ገዢ የነበረው የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ እስከ ዳዊት መቃብር (ከዳዊት መቃብር ትይዩ ጀምሮ)፥ እስከ ኩሬ፤ እስከ ጀግኖች ሰፈር ድረስ ያለውን ክፍል ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከርሱም በኋላ የቤትጹር አውራጃ እኩሌታ ገዥ የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ እስከ ዳዊት መቃብር ትይዩ እስከ ሰው ሠራሹ ኵሬና የጀግኖች ቤት ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ያለውን መልሶ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከእርሱም በኋላ የቤትጹር አውራጃ እኩሌታ ገዢ የሆነው የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ በዳዊት መቃብር ፊት ለፊት እስካለው ስፍራ፥ እስከ ተሠራው መዋኛ ስፍራና እስከ ኃያላኑ ቤት ድረስ አደሰ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከእ​ር​ሱም በኋላ የቤ​ሶር ግዛት እኩ​ሌታ ገዢ የዓ​ዛ​ቡህ ልጅ ነህ​ምያ በዳ​ዊት መቃ​ብር አን​ጻር እስ​ካ​ለው ስፍራ፥ እስከ ተሠ​ራ​ውም መዋኛ፥ እስከ ኀያ​ላ​ኑም ቤት ድረስ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ከእርሱም በኋላ የቤትጹር ግዛት እኩሌታ አለቃ የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ በዳዊት መቃብር አንጻር እስካለው ስፍራ፥ እስከ ተሠራውም መዋኛ፥ እስከ ኃያላኑም ቤት ድረስ አደሰ።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 3:16
18 Referencias Cruzadas  

ንጉሥ ሕዝቅያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ የጀግንነት ሥራው ጭምር፥ እንዲሁም የውሃ ማጠራቀሚያ ግድብ እንዴት እንደ ሠራና ወደ ከተማይቱ ውሃ ለማምጣት ያስቈፈረው የመሬት ውስጥ ቦይ አሠራር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።


ሻማይም ማዖንን ወለደ፤ ማዖንም ቤትጹርን ወለደ።


ቤትጹር፥ ሶኮ፥ ዐዱላም፥


ሬሳውም በልዩ ቅመማ ቅመምና በሽቶ ታሽቶ እርሱ ራሱ በዳዊት ከተማ ከአለት አስፈልፍሎ ባሠራው መቃብር ተቀበረ፤ ስለ ክብሩም ብዙ እንጨት ከምረው በማንደድ ታላቅ ለቅሶ አደረጉለት።


ቀጥሎም ከከተማይቱ በስተ ምሥራቅ በኩል በሰሜን ወደሚገኘው “የውሃ ምንጭ ቅጽር በር” ተብሎ በሚጠራው ስፍራና ወደ ንጉሡ ኲሬ ሄድኩ፤ ነገር ግን ተቀምጬበት የነበረው እንስሳ የፍርስራሹን ክምር ለማለፍ የሚያስችለው መንገድ ማግኘት አልቻለም።


ቀጥሎ ያለውንም ክፍል የሌላው የኢየሩሳሌም ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው የሀሎሔሽ ልጅ ሻሉም ሠራ፤ ሴቶች ልጆቹም ሥራውን ይረዱት ነበር።


የቤትሀካሬም ወረዳ ገዢ የሆነው የሬካብ ልጅ ማልኪያ የጒድፍ መጣያውን ቅጽር በር በማደስ ሠራ፤ በሮችን ገጠመ፤ ለበሮቹም ቊልፎችንና መወርወሪያዎችን አበጀ።


በቅጽሩ ሥራ ተካፋዮች የነበሩት ሌዋውያን ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፦ የባኒ ልጅ ረሑም ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ። የቀዒላ ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው ሐሻብያ ወረዳውን በመወከል ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ።


ከእነርሱም ቀጥሎ ያለውን ክፍል የኢየሩሳሌም ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው የሑር ልጅ ረፋያ ሠራ።


የሚያድጉ ዛፎችን ለማጠጣት የውሃ ግድቦችን ሠራሁ፤


እነሆ፥ የሰሎሞን ሠረገላ እየመጣች ነው፤ ከእስራኤል ኀያላን መካከል የተመረጡ ሥልሳ የክብር ዘበኞች አጅበዋታል፤


ከጥንቱ ኲሬ የሚወርደውን ውሃ ለመመለስ በከተማይቱ ውስጥ ግድብ ሠራችሁ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በመጀመሪያ ዐቅዶ ያደረገው እግዚአብሔር መሆኑ ትዝ አላላችሁም።


የዳዊት ከተማ ብዙ ፍርስራሾች መብዛታቸውን ተመልክታችኋል፤ ከታችኛውም ኩሬ ውሃ አጠራቀማችሁ።


እግዚአብሔርም ኢሳይያስን እንዲህ አለው፦ “አንተና ልጅህ ሼርያሹብ ንጉሥ አካዝን ለመገናኘት ውጡ፤ እርሱንም ከላይኛው ኩሬ ውሃ በሚመጣበት በልብስ አጣቢዎች ቦታ ታገኙታላችሁ።


“ወንድሞቼ ሆይ! ከቀድሞ አባቶች አንዱ የሆነው ዳዊት እንደ ሞተና እንደ ተቀበረ፥ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ እንዳለ በግልጥ ልንገራችሁ።


እንዲሁም ሐልሑል፥ ቤትጹር፥ ጌዶር፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos