ነህምያ 12:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባቅቡቅያ፥ ዑኖና ሌሎችም ሌዋውያን ወንድሞቻቸው ከእነርሱ ጋር በመቀባበል ይዘምሩ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞቻቸው የሆኑት በቅቡቅያና ዑኒም በአገልግሎት ጊዜ ከእነርሱ ትይዩ ይቆሙ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞቻቸው ባቅቡቅያና ዑኖ በአገልግሎቱ ጊዜ በፊት ለፊታቸው ይቆሙ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቻቸውም በቅቡቅያና ዑኒ በየሰሞናቸው በአንጻራቸው ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞቻቸውም በቅቡቅያና ዑኒ በየሰሞናቸው በአንጻራቸው ነበሩ። |
ሌዋውያኑ በሐሻብያ፥ በሼሬብያ፥ በኢያሱ፥ በቢኑይና በቃድሚኤል መሪነት በሁለት ቡድኖች ተከፈሉ። ሁለቱም ቡድኖች የእግዚአብሔር ሰው የሆነ ንጉሥ ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እየተቀባበሉ የምስጋና መዝሙር በማቅረብ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።