እኔም ነህምያ የይሁዳን መሪዎች በቅጽሩ ላይ እንዲወጡ ካደረግሁ በኋላ ሁለት ታላላቅ የመዘምራን ቡድን የምስጋና መዝሙር እንዲዘምሩ አደረግሁ፤ የመጀመሪያው ቡድን በቅጽሩ ግንብ አናት ላይ በስተቀኝ በኩል ወደሚገኘው ወደ ጒድፍ መጣያው የቅጽር በር በኩል አለፈ፤
ነህምያ 12:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌላው የመዘምራን ቡድን ሰልፍ የቅጽሩን ግንብ ጫፍ በመከተል ወደ ግራ በኩል አለፈ፤ እኔም ከሕዝቡ እኩሌታ ጋር ይህንኑ የቡድን ሰልፍ እከተል ነበር፤ የእቶኑንም ግንብ አልፈን ወደ ሰፊው ቅጽር ግንብ ደረስን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምስጋና የሚያቀርቡት ሁለተኛው ቡድን በስተግራ በኩል ሄደ፤ እኔም ከከፊሉ ሕዝብ ጋራ ሆኜ በቅጥሩ ግንብ ላይ፣ የእቶኑን ግንብ በማለፍ እስከ ሰፊው ቅጥር ተከተልኋቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፊት ይሄድ የነበረው ሁለተኛው የምስጋና መዘምራን ክፍል ነበር፤ እኔና የሕዝቡ እኩሌታ በስተ ኋላቸው ነበርን፤ በቅጥሩም ላይ፥ ከ “የእቶኑ ግንብ” በላይ እስከ “ሰፊው ቅጥር” ድረስ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለተኛውም የአመስጋኞቹ ክፍል ወደ ግራ ሄደ፤ እኔና የሕዝቡም እኩሌታ በስተኋላቸው ነበርን፤ በቅጥሩም ላይ፥ በእቶኑ ግንብ በላይ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለተኛውም የአመስጋኞቹ ተርታ ወደ ግራ ሄደ፥ እኔና የሕዝቡም እኩሌታ በስተኋላቸው ነበርን፥ በቅጥሩም ላይ፥ በእቶኑ ግንብ በላይ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ፥ ከኤፍሬምም በር በላይ፥ |
እኔም ነህምያ የይሁዳን መሪዎች በቅጽሩ ላይ እንዲወጡ ካደረግሁ በኋላ ሁለት ታላላቅ የመዘምራን ቡድን የምስጋና መዝሙር እንዲዘምሩ አደረግሁ፤ የመጀመሪያው ቡድን በቅጽሩ ግንብ አናት ላይ በስተቀኝ በኩል ወደሚገኘው ወደ ጒድፍ መጣያው የቅጽር በር በኩል አለፈ፤
ወርቅ አንጣሪው የሐርሃያ ልጅ ዑዝኤል ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ። ቀጥሎ ያለውንም ክፍል ሽቶ ቀማሚው ሐናንያ ሠራ፤ እነዚህ ሰዎች ኢየሩሳሌምን “ሰፊው ቅጽር” ተብሎ እስከሚጠራው ስፍራ ድረስ ያለውን ሁሉ ሠሩ።