ነህምያ 11:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሎድና፥ ኦኖ፥ እንዲሁም “የእጅ ጥበብ ሠራተኞች ሸለቆ” ተብሎ የሚጠራው ስፍራ ሁሉ የእነርሱ መኖሪያዎች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሎድና በኦኖ፣ ደግሞም ጌሃርሻም በተባለው ስፍራ ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሎድና በእጀ ጠቢባን ሸለቆ በኦኖ ተቀመጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሎድ፥ በኣውኖ፥ በጌሐራሲም ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስቦይም፥ በንበላት፥ በሎድ፥ በኦኖ፥ በጌሐራሺም ተቀመጡ። |
ኤልፓዓልም ዔቤር፥ ሚሸዓምና ሼሜድ ተብለው የሚጠሩ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ሼሜድም ኦኖና ሎድ ተብለው የሚጠሩትን ከተሞችና በዙሪያቸው የሚገኙትን መንደሮች የሠራ ነው።
ከዚህም የተነሣ ሰንባላጥና ጌሼም በተለይ ኦኖ ተብሎ በሚጠራው ሜዳ ከሚገኙት መንደሮች በአንዲቱ እንድንገናኛቸው መልእክት ላኩብኝ፤ ይህም እኔን ለመጒዳት በተንኰል የተዶለተ ዘዴ ነበር።