Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 9:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ጴጥሮስ በየአገሩ ሲዘዋወር ሳለ በልዳ ወደሚኖሩት ምእመናን ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ጴጥሮስም ከአገር ወደ አገር በሚዘዋወርበት ጊዜ፣ በልዳ የሚኖሩትን ቅዱሳን ለመጐብኘት ወረደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ጴጥሮስም በየስፍራው ሁሉ ሲዞር በልዳ ወደሚኖሩ ቅዱሳን ደግሞ ወረደ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ከዚ​ህም በኋላ ጴጥ​ሮስ በየ​ቦ​ታዉ ሲዘ​ዋ​ወር በልዳ ወደ​ሚ​ኖ​ሩት ቅዱ​ሳን ዘንድ ደረሰ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ጴጥሮስም በየስፍራው ሁሉ ሲዞር በልዳ ወደሚኖሩ ቅዱሳን ደግሞ ወረደ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 9:32
18 Referencias Cruzadas  

ሐናንያ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ጌታ ሆይ! ይህ ሰው በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ምእመናንህ ላይ ብዙ ክፉ ነገር ማድረጉን ከብዙዎች ሰምቻለሁ።


ጴጥሮስና ዮሐንስ ከመሰከሩና የጌታንም ቃል ከተናገሩ በኋላ በብዙ የሰማርያ መንደሮች ወንጌልን እያበሠሩ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።


የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋዮች ከሆኑት ከጳውሎስና ከጢሞቴዎስ፥ በፊልጵስዩስ ከተማ ለሚኖሩ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳን ለሆኑ ሁሉ፥ እንዲሁም ለኤጲስ ቆጶሳትና ዲያቆናት፦


በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ታማኞች ለሆኑት፥ በኤፌሶን ለሚገኙት ቅዱሳን፥


ስለዚህ በሮም ለምትኖሩ፥ እግዚአብሔር ለወደዳችሁና ወገኖቹ እንድትሆኑ ለጠራችሁ ሁሉ፦ ከአባታችን ከእግዚአብሔርና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።


በኢየሩሳሌም ያደረግኹትም ይህንኑ ነበር፤ ከካህናት አለቆች በተቀበልኩት ሥልጣን ከምእመናን ብዙዎቹ ወደ ወህኒ ቤት እንዲገቡ አድርጌአለሁ፤ ሲገድሉአቸውም ከገዳዮቻቸው ጋር ተስማምቻለሁ።


እርሱም እጁን ዘርግቶ ያዘና አስነሣት፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶችና ሌሎችንም አማኞች ጠርቶ ልጅቷን በሕይወት በፊታቸው አቀረባት።


በኢየሩሳሌም የነበሩት ሐዋርያት የሰማርያ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል መቀበላቸውን በሰሙ ጊዜ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ወደ ሰማርያ ላኩአቸው።


ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም፥ በይሁዳ ምድር ሁሉ፥ በሰማርያ፥ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”


መቃብሮችም ተከፍተው ሞተው ከነበሩት ቅዱሳን ሰዎች ብዙዎች ከሞት ተነሡ።


የፍትሕን ሂደት ይከታተላል፤ በታማኝነት የሚያገለግሉትንም ይጠብቃል።


በምድር ላይ የሚኖሩ ቅዱሳን የተከበሩ ናቸው፤ በእነርሱም እደሰታለሁ።


ኤልፓዓልም ዔቤር፥ ሚሸዓምና ሼሜድ ተብለው የሚጠሩ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ሼሜድም ኦኖና ሎድ ተብለው የሚጠሩትን ከተሞችና በዙሪያቸው የሚገኙትን መንደሮች የሠራ ነው።


ሎድና፥ ኦኖ፥ እንዲሁም “የእጅ ጥበብ ሠራተኞች ሸለቆ” ተብሎ የሚጠራው ስፍራ ሁሉ የእነርሱ መኖሪያዎች ነበሩ።


እዚያም ስምንት ዓመቶች ሙሉ በአልጋ ላይ የተኛ ኤኒያ የሚባለውን ሽባ አገኘ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios