ናሆም 3:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአለንጋና የመንኰራኲሮች ድምፅ፥ የፈረስ ግልቢያና የሠረገላ መንጓጓት ይሰማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጅራፍ ድምፅ፣ የመንኰራኵር ኳኳቴ፣ የፈጣን ፈረስ ኰቴ፣ የሠረገሎች ድምፅ ተሰምቷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጅራፍ ድምፅ፥ የመንኰራኵር ድምፅ፥ የፈረስ ኮቴ፥ የሠረገላ መንጓጓት ተሰምቶአል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአለንጋ ድምፅ፥ የመንኰራኵርም ድምፅ፥ የፈረሶችም ኮቴ፥ የፈጣን ሰረገላም ጩኸት ተሰምቶአል፣ |
ከሚጋልቡ ፈረሶች ኮቴ ድምፅ፥ ከጠላት መንኰራኲር ድምፅ፥ ከሠረገሎቻቸው መትመም የተነሣ አባቶች ኀይላቸው በመድከሙ ምክንያት ልጆቻቸውን እንኳ ለመርዳት ወደ ኋላ አይመለሱም።
እንደ ሠረገላ ድምፅ እያሰሙ በተራሮች ጫፍ ላይ ይዘላሉ፤ ገለባን እንደሚያቃጥል እሳትም፥ ሁሉን ነገር ያቃጥላሉ፤ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ብርቱ ሠራዊት በሰልፍ ይተማሉ።