ሕዝቅያስ ‘አምላካችን እግዚአብሔር ከአሦራውያን እጅ ያድነናል’ ይላችኋል፤ ነገር ግን እርሱ እንደዚህ ባለ አነጋገር እያታለለ፥ በራብና በውሃ ጥም እንድታልቁ ሊያደርጋችሁ ነው፤
ናሆም 3:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቶችሽ ከበው በሚያስጨንቁሽ ጊዜ የምትጠጪውን ውሃ ቀድተሽ አዘጋጂ! ምሽጎችሽን አጠናክሪ! ጭቃ ረግጠሽ የሸክላ መሥሪያ አዘጋጂ! ጡብም ሥሪ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለከበባው ውሃ ቅጅ፤ መከላከያሽን አጠናክሪ፤ የሸክላውን ዐፈር ፈልጊ፤ ጭቃውን ርገጪ፤ ጡቡንም ሥሪ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለከበባው ውኃ ለራስሽ ቅጂ፥ ምሽግሽን አጠናክሪ፤ ወደ ጭቃው ግቢ፥ ጭቃውንም ርገጪ፥ የጡብ መሥሪያ ያዢ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብበው ያስጨንቁሻልና ውኃን ቅጂ፣ አምባሽን አጠንክሪ፣ ወደ ጭቃ ገብተሽ እርገጪ፣ የጡብን መሠሪያ ያዢ። |
ሕዝቅያስ ‘አምላካችን እግዚአብሔር ከአሦራውያን እጅ ያድነናል’ ይላችኋል፤ ነገር ግን እርሱ እንደዚህ ባለ አነጋገር እያታለለ፥ በራብና በውሃ ጥም እንድታልቁ ሊያደርጋችሁ ነው፤
እናንተ አሕዛብ ጦርነትን ዐወጁ! ነገር ግን ትደመሰሳላችሁ፤ እናንተም የሩቅ አገር ሰዎች ሁሉ አድምጡ፤ ለጦርነትም ተዘጋጁ! ነገር ግን ትደመሰሳላችሁ፤ አሁንም ለጦርነት ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ትደመሰሳላችሁ።
ፈረሶች ወደ ፊት እንዲሄዱ፥ ሠረገሎችም አስደንጋጭ በሆነ ፍጥነት እንዲሽከረከሩ እዘዙ፤ ከኢትዮጵያና ከሊቢያ ጋሻቸውን አንግበው በመጡ ሰዎችና፥ ከልድያ በመጡ ቀስት በሚወረውሩ ኀያላን ሰዎች ጭምር የተጠናከሩ ወታደሮችን ላኩ” ይላል እግዚአብሔር።
ነነዌ ሆይ! አደጋ ጣይ መጥቶብሻል! ስለዚህ ምሽጎችሽን አጠናክሪ! አውራ መንገዱን ሁሉ ጠብቂ! ወገብሽን ታጠቂ! ኀይልሽንም ሁሉ አጠናክሪ!