“እግዚአብሔር ክፉ አድራጊዎች ከቶ አያስተውሉምን? ሰዎች እንጀራን እንደሚበሉ ክፉ አድራጊዎች ሕዝቤን ይበዘብዛሉ፤ እነርሱም ወደ እኔ ወደ እግዚአብሔር አይጸልዩም።” ይላል።
ሚክያስ 3:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሕዝቤን ቆዳ ገፋችሁ አጥንታቸውን ቈራርጣችሁ ለአፍላልና ለድስት እንደሚቈራረጥ ሥጋ አደረጋችኋቸው፤ ሥጋቸውንም በላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሕዝቤን ሥጋ በላችሁ፤ ቈዳቸውን ገፈፋችሁ፤ ዐጥንቶቻቸውንም ሰባበራችሁ፤ በመጥበሻ እንደሚጠበስ፣ በድስት እንደሚቀቀል ሥጋ ቈራረጣችኋቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሕዝቤን ሥጋ በሉ፥ ቁርበታቸውን ከላያቸው ላይ ገፈፉ፥ አጥንታቸውን ሰበሩ፤ በአፍላል እንዳለ በድስትም ውስጥ እንደሚከተት ሥጋ ቆራርጠዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሕዝቤን ሥጋ በልታችኋል፥ ቁርበታቸውንም ገፍፋችኋቸዋል፥ አጥንታቸውንም ሰብራችኋል፥ ለአፍላል እንደሚሆን ሥጋ ለድስትም እንደሚሆን ሙዳ ቈራረጣችኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሕዝቤን ሥጋ በልታችኋል፥ ቁርበታቸውንም ገፍፋችኋቸዋል፥ አጥንታቸውንም ሰብራችኋል፥ ለአፍላል እንደሚሆን ሥጋ ለድስትም እንደሚሆን ሙዳ ቈራረጣችኋቸው። |
“እግዚአብሔር ክፉ አድራጊዎች ከቶ አያስተውሉምን? ሰዎች እንጀራን እንደሚበሉ ክፉ አድራጊዎች ሕዝቤን ይበዘብዛሉ፤ እነርሱም ወደ እኔ ወደ እግዚአብሔር አይጸልዩም።” ይላል።
ስለዚህ የሕዝቡን መሪዎችና አማካሪዎች ወደ ፍርድ አቅርቦ እንዲህ ይላቸዋል፦ “የወይኑን አትክልት ቦታ ዘረፋችሁ፤ ከድኾች በተዘረፈው ሀብትም ቤታችሁን ሞላችሁ።
‘እንደገና መልሰን ቤቶችን የምንሠራበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፤ ከተማይቱ እንደ ሥጋ መቀቀያ ሰታቴ ስትሆን፥ እኛ ደግሞ በውስጥዋ እንደ ሥጋ ሆነናል’ ብለዋል።
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል፦ “በሕዝቤ ላይ በጠላትነት ተነሥታችኋል፤ ከጦርነት ተመልሰው በመተማመን በመካከላችሁ የሚያልፉትን ሰላማዊ ሰዎች ገፈፋችሁ፤