ሚክያስ 2:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድሩ ተመልሶ ለእግዚአብሔር ሕዝብ በሚሰጥበት ጊዜ እናንተ ምንም ድርሻ አይኖራችሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በእግዚአብሔር ጉባኤ ውስጥ፣ መሬት በዕጣ ገመድ የሚያካፍል ማንም አይኖርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በጌታ ጉባኤ መካከል በዕጣ ገመድ የሚጥል አይኖርህም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ በእግዚአብሔር ጉባኤ መካከል በዕጣ ገመድ የሚጥል አይኖርህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በእግዚአብሔር ጉባኤ መካከል በዕጣ ገመድ የሚጥል አይኖርህም። |
ቴልሜላሕ፥ ቴልሐርሻ፥ ከሩብ፥ አዶንና ኢሜር ተብለው ከሚጠሩት የገጠር ከተሞች የተመለሱ የደላያ፥ የጦቢያና የነቆዳ ጐሣዎች ወገኖች የሆኑት ዘሮች ድምር 642 ነበር፤ ይሁን እንጂ እነዚህ ሁሉ የእስራኤል ዘሮች መሆናቸውን ለማወቅ የሚያስችል በቂ ማስረጃ አልነበራቸውም።
የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር በሰጣቸው ምድር አይኖሩም፤ ነገር ግን ተገደው ወደ ግብጽ ይመለሳሉ፤ ወደ አሦርም ሄደው በሥርዓት ንጹሕ ያልሆነ ምግብ ይበላሉ።
“ከጋብቻ ውጪ ዲቃላ ሆኖ የተወለደና የእርሱም ዘር ሆኖ የተወለደ ሁሉ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳ ወደ እግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ ገብቶ አይቈጠር።
ልዑል እግዚአብሔር ለሕዝቡ ርስታቸውን ባከፋፈለ ጊዜ፥ የሰውን ዘር በለያየ ጊዜ፥ እንደ እስራኤል ልጆች ቊጥር ብዛት፥ ለሕዝቡ ድንበርን ሠራላቸው።
ከእያንዳንዱ ነገድ ሦስት ሦስት ሰዎች ምረጡልኝ፤ እኔም እያንዳንዱ ነገድ ማግኘት የሚገባውን የርስት ድርሻ ለማወቅ የምድሪቱን ሁኔታ አጥንተው እንዲመዘግቡ በመላ አገሪቱ እልካቸዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሰው ወደ እኔ ይመጣሉ።