ማቴዎስ 7:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ተናግሮ ባበቃ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርቱ ተደነቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ማስተማሩን በፈጸመ ጊዜ፣ ሕዝቡ በትምህርቱ ተደነቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ ይህንን ንግግር በጨረሰ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም ይህን ነገር በጨረሰ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፤ እንደ ጻፎቻቸው ሳይሆን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ይህን ነገር በጨረሰ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፤ እንደ ጻፎቻቸው ሳይሆን፥ |
ኢየሱስ እነዚህን ትእዛዞች ለዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ከሰጠ በኋላ ያን ቦታ ትቶ በአቅራቢያው ወደሚገኙት ከተሞች ሊሰብክና ሊያስተምር ሄደ።
የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ይህን ሲናገር ሰሙት፤ ሕዝቡም ሁሉ በትምህርቱ ይደነቁ ስለ ነበር ፈሩት፤ ስለዚህ እንዴት አድርገው እንደሚያጠፉት ዘዴ ይፈልጉ ነበር።
በሰንበት ቀን በምኲራብ ማስተማር ጀመረ፤ ብዙ ሰዎች በዚያ ተገኝተው ይሰሙት ነበር፤ እነርሱም “ይህ ሰው ይህን ሁሉ ነገር ከየት አገኘው? ምን ዐይነት ጥበብ ተሰጥቶታል? እነዚህንስ ተአምራት የሚያደርገው እንዴት ነው?” እያሉ ይደነቁ ነበር።