አብራም 99 ዓመት በሆነው ጊዜ እግዚአብሔር ተገለጠለትና “እኔ ኤልሻዳይ ሁሉን የምችል አምላክ ነኝ፤ ለእኔ በመታዘዝ ዘወትር ትክክል የሆነውን ነገር አድርግ፤
ማቴዎስ 5:48 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹሞች ሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ። |
አብራም 99 ዓመት በሆነው ጊዜ እግዚአብሔር ተገለጠለትና “እኔ ኤልሻዳይ ሁሉን የምችል አምላክ ነኝ፤ ለእኔ በመታዘዝ ዘወትር ትክክል የሆነውን ነገር አድርግ፤
እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ እኔ ቅዱስ ስለ ሆንኩ እናንተም ራሳችሁን የተቀደሰ አድርጉ፤ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱትን ነፍሳት በመብላት ራሳችሁን አታርክሱ።
ይህን ብታደርጉ፥ በሰማይ ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆናላችሁ። እርሱ ለክፉዎችና ለደጎች ፀሐዩን ያወጣል፤ እንዲሁም ለጻድቃንና ለግፈኞች ዝናቡን ያዘንባል።
በተረፈውስ ወንድሞቼ ሆይ! ደኅና ሁኑ! አኗኗራችሁን አስተካክሉ፤ ምክሬን ተከተሉ፤ እርስ በእርሳችሁ ተስማሙ፤ በሰላምም ኑሩ፤ የፍቅርና የሰላም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
እንግዲህ ወዳጆቼ ሆይ፥ ይህ ሁሉ ተስፋ የተሰጠው ለእኛ ስለ ሆነ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ከማናቸውም ነገር ራሳችንን እናንጻ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ቅድስናችን ፍጹም እንዲሆን እናድርግ።
እያንዳንዱ ሰው በክርስቶስ ብቁ ሰው እንዲሆን አድርገን ለማቅረብ ለሰው ሁሉ ጥበብን ሁሉ በማስተማርና በመምከር ስለ ክርስቶስ እንሰብካለን።
የእናንተ ወገን የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ኤጳፍራም ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በመንፈሳዊ ሕይወት በማደግ ጸንታችሁ እንድትቆሙና የእግዚአብሔርንም ፈቃድ በሙሉ እንድትፈጽሙ እርሱ ስለ እናንተ በጸሎቱ ዘወትር ይጸልያል።