መሎጊያዎቹ እጅግ ረጃጅሞች ስለ ነበሩ በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት የቆመ ማንኛውም ሰው ሊያያቸው ይችላል፤ በሌላ አቅጣጫ የቆመ ግን ፈጽሞ ሊያያቸው አይችልም ነበር፤ እነዚህ መሎጊያዎች እስከ ዛሬ ድረስ በዚያው ይገኛሉ፤
ማቴዎስ 27:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ምክንያት ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ “የደም መሬት” እየተባለ ይጠራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ያ ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ “የደም መሬት” ተብሎ ይጠራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም ምክንያት ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተብሎ ይጠራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ “የደም መሬት” ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ። |
መሎጊያዎቹ እጅግ ረጃጅሞች ስለ ነበሩ በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት የቆመ ማንኛውም ሰው ሊያያቸው ይችላል፤ በሌላ አቅጣጫ የቆመ ግን ፈጽሞ ሊያያቸው አይችልም ነበር፤ እነዚህ መሎጊያዎች እስከ ዛሬ ድረስ በዚያው ይገኛሉ፤
ይህም ነገር በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ ታወቀ፤ ስለዚህ ያ መሬት በቋንቋቸው ‘አኬልዳማ’ ተብሎ ተጠራ፤ ትርጓሜውም ‘የደም መሬት’ ማለት ነው።
እግዚአብሔርም ከቤትፐዖር ከተማ ፊት ለፊት በሞአብ አገር በሚገኘው ሸለቆ ቀበረው፤ ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ እርሱ የተቀበረበትን ትክክለኛ ቦታ ለይቶ የሚያውቅ የለም።
ኢያሱም ደግሞ ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው በቆሙበት በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ዐሥራ ሁለት የመታሰቢያ ድንጋዮችን አቆሙ፤ እነዚያም ድንጋዮች እስከ ዛሬ በዚያው ይገኛሉ፤