La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 26:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያም ኢየሱስ በማእድ ተቀምጦ ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ ሽቶ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ሽቶውንም በራሱ ላይ አፈሰሰችው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ አንድ ብልቃጥ የአልባስጥሮስ ሽቱ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች፤ በማእድ ላይ ተቀምጦ ሳለም በራሱ ላይ አፈሰሰችው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በማዕድም ተቀምጦ ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቶ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች፤ በራሱ ላይም አፈሰሰችው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቱ የሞላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች፤ በማዕድም ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቱ የሞላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች በማዕድም ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 26:7
12 Referencias Cruzadas  

በዚያን ጊዜ ነቢዩ ኤልሳዕ ደቀ መዛሙርቱ ከሆኑት ነቢያት አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለ፤ “በገለዓድ ወደምትገኘው ወደ ራሞት ለመሄድ ተዘጋጅ፤ ይህንንም የዘይት ማሰሮ ያዝ፤


በአሮን ራስና ጢም ላይ እንደሚፈስስ፥ እስከ ልብሱም ዘርፍ ድረስ እንደሚዘልቅ፥ መልካም መዓዛ እንዳለው የወይራ ዘይት ነው።


የሞቱ ዝንቦች ተቀምሞ የተሠራውን የዘይት ሽቶ ሊያገሙት ይችላሉ፤ እንዲሁም ትንሽ ሞኝነት ታላቅ ጥበብን ያጠፋል።


ሁልጊዜ ነጭ ልብስ ለብሰህ ጠጒርህን ተቀባ።


የምትቀባው ሽቱ መልካም መዓዛ አለው፤ ስምህን መጥራት ሽቱን እንደ መርጨት ነው፤ ቈነጃጅትም የሚያፈቅሩህ ስለዚህ ነው።


ብዙ ዘይትና ሽቶ ተቀብታችሁ ሞሌክ ወደ ተባለው ጣዖት ሄዳችሁ፤ የምታመልኳቸውን ጣዖቶች ለመፈለግ መልእክተኞቻችሁን ወደ ሩቅ ቦታ ወደ ሙታን ዓለም እንኳ ሳይቀር ላካችሁ።


ደቀ መዛሙርቱ ይህን አይተው ተቈጡና እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሽቶ ለምን በከንቱ ባከነ?


ኢየሱስ በቢታንያ ለምጻም በነበረው በስምዖን ቤት ነበር። በገበታም ቀርቦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነና የከበረ የናርዶስ ሽቶ የሞላበት፥ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች፤ ብልቃጡን ሰብራ ሽቶውን በኢየሱስ ራስ ላይ አፈሰሰችው።


አንተ ራሴን ዘይት እንኳ አልቀባኸኝም፤ እርስዋ ግን እግሮቼን ሽቶ ቀባች፤