ቀናኢው ስምዖን፥ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ። አንዱ አስተያየት፥ ከቦታ ወይም ከሀገር ጋር ሲያያይዘው ሌላው ወገን ደግሞ ይሁዳን ውሸታም ወይም አታላይ ብሎ ለመስደብ የተሰጠ ቅጽል ነው ይላል።
ማቴዎስ 26:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው አስቀሮታዊው ይሁዳ ወደ ካህናት አለቆች ሄደና አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ የተባለው ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ የሚባለው ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜ የአስቆሮቱ ይሁዳ የሚባለው ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ የአስቆሮቱ ይሁዳ የሚባለው ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ፦ |
ቀናኢው ስምዖን፥ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ። አንዱ አስተያየት፥ ከቦታ ወይም ከሀገር ጋር ሲያያይዘው ሌላው ወገን ደግሞ ይሁዳን ውሸታም ወይም አታላይ ብሎ ለመስደብ የተሰጠ ቅጽል ነው ይላል።
ኢየሱስ ገና ሲናገር ሳለ እነሆ፥ ከዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት አንዱ የሆነው ይሁዳ መጣ፤ ከእርሱም ጋር ሰይፍና ዱላ የያዙ ብዙ ሰዎች መጡ፤ እነርሱ ከካህናት አለቆችና ከሕዝብ ሽማግሌዎች የተላኩ ነበሩ።
ኢየሱስ እንደተፈረደበት ባየ ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ተጸጸተ፤ ሠላሳውንም ጥሬ ብር ለካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች እንዲህ በማለት መልሶ ሰጣቸው፤
ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ራት ይበሉ ነበር፤ የስምዖን ልጅ አስቆሮታዊው ይሁዳ ግን ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ ዲያብሎስ በልቡ ክፉ ሐሳብ አሳደረበት።
ኢየሱስም “እርሱ ይህን እንጀራ በወጥ አጥቅሼ የማጐርሰው ነው” አለ። ይህንንም ብሎ እንጀራ በወጥ አጠቀሰና የአስቆሮታዊው ስምዖን ልጅ ለሆነው ለይሁዳ አጐረሰው።
“ወንድሞች ሆይ፥ ኢየሱስን ለያዙት ሰዎች መሪ ስለ ሆናቸው ስለ ይሁዳ፥ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል መፈጸም ነበረበት።