ማቴዎስ 24:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከ መጨረሻ በትዕግሥት የሚጸና ግን ይድናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስከ መጨረሻው የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። |
በመልካም መሬት ላይ የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ግን በመልካምና በቅን ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁትን ነው፤ እነርሱ በቃሉ ጸንተው ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።”
ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ታማኝ የሆነው እንደ ልጅ ሆኖ ነው፤ ቤቱም እኛ ነን፤ ቤቱ የምንሆነውም የምንተማመንበትን ነገርና የምንመካበትን ተስፋ አጽንተን ስንይዝ ነው።
ወደ ፊት የሚደርስብህን መከራ አትፍራ፤ እነሆ፥ እንድትፈተኑ ከእናንተ አንዳንዶቹን ዲያብሎስ ወደ እስር ቤት ያገባችኋል፤ ዐሥር ቀንም መከራ ትቀበላላችሁ፤ እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ የሕይወት አክሊል እሰጥሃለሁ።