ማቴዎስ 21:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጁንም ይዘው ከወይን አትክልቱ ቦታ ውጪ ወሰዱና ገደሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይዘውም ከወይኑ ዕርሻ ውጭ አውጥተው ገደሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይዘውም ከወይኑ አትክልት ሥፍራ አውጥተው ገደሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይዘውም ከወይኑ አትክልት አወጡና ገደሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይዘውም ከወይኑ አትክልት አወጡና ገደሉት። |
እርሱም ራሱ እግዚአብሔር አስቀድሞ ባቀደውና ባወቀው አሠራር መሠረት ለእናንተ ተላልፎ ተሰጠ፤ እናንተም በዐመፀኞች እጅ እንዲሰቀልና እንዲሞት አደረጋችሁት።
ይህ ሰው ድኖ በፊታችሁ የቆመው እናንተ በሰቀላችሁትና እግዚአብሔር ግን ከሞት ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንደ ሆነ ለእናንተ ለሁላችሁና ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን።
ከነቢያት መካከል አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን አለ? እነርሱ የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ እናንተም አሁን ይህን ጻድቁን አሳልፋችሁ በመስጠት ገደላችሁት።