በሕዝቦች ዘንድ በጣም ለተናቅህና ለተጠላህ፥ ለገዢዎችም አገልጋይ ለሆንክ ለአንተ፥ አዳኙ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ነገሥታት ሲያዩህ ይነሡልሃል፤ ልዑላንም ይሰግዱልሃል፤ ይህም የሚሆነው በመረጠህ በታማኙ በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ምክንያት ነው።”
ማቴዎስ 13:57 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ምክንያት ተሰናክለውበት ሳይቀበሉት ቀሩ። ኢየሱስ ግን፦ “ነቢይ የማይከበረው በሀገሩና በገዛ ቤቱ ብቻ ነው” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም የተነሣ ተሰናከሉበት። ኢየሱስ ግን፣ “ነቢይ የማይከበረው በራሱ አገርና በራሱ ቤት ብቻ ነው” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተሰናከሉበትም። ኢየሱስ ግን “ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በስተቀር ሳይከበር አይቀርም፤” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስ ግን “ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም፤” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስ ግን፦ ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው። |
በሕዝቦች ዘንድ በጣም ለተናቅህና ለተጠላህ፥ ለገዢዎችም አገልጋይ ለሆንክ ለአንተ፥ አዳኙ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ነገሥታት ሲያዩህ ይነሡልሃል፤ ልዑላንም ይሰግዱልሃል፤ ይህም የሚሆነው በመረጠህ በታማኙ በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ምክንያት ነው።”
እርሱም በሌሎች የተናቀና የተጠላ ነበር፤ እርሱ የመከራና የሐዘን ሰው ነበር። ሰዎች ፊታቸውን እስኪያዞሩበት ድረስ እርሱ የተናቀ፥ እኛም ያላከበርነው ሰው ነበር።
የኢየሱስ ዝና በሁሉም ዘንድ ስለ ታወቀ፥ ንጉሡ ሄሮድስ ስለ እርሱ ሰማ። አንዳንድ ሰዎች፥ “መጥምቁ ዮሐንስ ከሞት ተነሥቶአል፤ ስለዚህ ይህ ሁሉ ተአምራት በእርሱ ይደረጋል” ይሉ ነበር።
ቀጥለውም “ለመሆኑ ይህ እንጨት ጠራቢው የማርያም ልጅ አይደለምን? የያዕቆብ፥ የዮሳ የይሁዳና የስምዖን ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ እዚህ ከእኛ ጋር አይደሉምን?” እያሉ በመናቅ ሳይቀበሉት ቀሩ።
እንዲህም አሉ፦ “ይህ የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለምን? አባቱንና እናቱንስ እናውቃቸው የለምን? ታዲያ፥ አሁን እርሱ እንዴት ‘ከሰማይ ወረድኩ’ ይላል?”