ማቴዎስ 11:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ እነዚህን ትእዛዞች ለዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ከሰጠ በኋላ ያን ቦታ ትቶ በአቅራቢያው ወደሚገኙት ከተሞች ሊሰብክና ሊያስተምር ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ለዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ትእዛዙን ሰጥቶ ከጨረሰ በኋላ፣ ለማስተማርና ለመስበክ ወደ ገሊላ ከተሞች ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ማዘዝ በፈጸመ በኋላ፥ በከተሞቻቸው ሊያስተምርና ሊሰብክ ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ማዘዝ በፈጸመ ጊዜ በከተሞቻቸው ሊያስተምርና ሊሰብክ ከዚያ አለፈ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ማዘዝ በፈጸመ ጊዜ በከተሞቻቸው ሊያስተምርና ሊሰብክ ከዚያ አለፈ። |
ኢየሱስም በምኲራቦቻቸው እያስተማረና የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል እየሰበከ፥ በልዩ ልዩ በሽታና ደዌ የተያዙትንም ሰዎች እየፈወሰ በገሊላ ምድር ሁሉ ይዘዋወር ነበር።
ኢየሱስም በምኲራቦቻቸው እያስተማረ፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከ፥ ሕዝቡን ከበሽታና ከደዌ ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተሞችና በመንደሮች ሁሉ ይዘዋወር ነበር።
ከዚህም በኋላ ኢየሱስ በየከተማውና በየመንደሩ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበከና የምሥራች እያበሠረ ያልፍ ነበር፤ ዐሥራ ሁለቱም አብረውት ነበሩ።
ወደ ሰማይ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ የሠራውን ነው፤ ወደ ሰማይ ያረገውም ለመረጣቸው ሐዋርያት ትእዛዙን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ከሰጣቸው በኋላ ነው፤
“ደግሞም እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ እንደ ቀባውና ኀይልም እንደ ሰጠው ታውቃላችሁ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ እርሱን መልካም ነገርን እያደረገና በዲያብሎስ የተያዙትን ሁሉ እየፈወሰ ተዘዋወረ።
ወንድሞች ሆይ! ሥራ ፈት ከሆነውና ከእኛ በተላለፈላችሁ ትውፊት መሠረት ከማይኖር ክርስቲያን ሁሉ እንድትለዩ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።