Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማቴዎስ 11:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ኢየሱስ ለዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ትእዛዙን ሰጥቶ ከጨረሰ በኋላ፣ ለማስተማርና ለመስበክ ወደ ገሊላ ከተሞች ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ማዘዝ በፈጸመ በኋላ፥ በከተሞቻቸው ሊያስተምርና ሊሰብክ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ኢየሱስ እነዚህን ትእዛዞች ለዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ከሰጠ በኋላ ያን ቦታ ትቶ በአቅራቢያው ወደሚገኙት ከተሞች ሊሰብክና ሊያስተምር ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ኢየሱስም ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ማዘዝ በፈጸመ ጊዜ በከተሞቻቸው ሊያስተምርና ሊሰብክ ከዚያ አለፈ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ኢየሱስም አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ማዘዝ በፈጸመ ጊዜ በከተሞቻቸው ሊያስተምርና ሊሰብክ ከዚያ አለፈ።

Ver Capítulo Copiar




ማቴዎስ 11:1
19 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስና በኀይል ቀባው፤ እርሱም እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ ስለ ነበረ በደረሰበት ሁሉ መልካም እያደረገ በዲያብሎስ ሥልጣን ሥር የነበሩትን ሁሉ ፈወሰ።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል እየሰበከ በየከተማውና በየመንደሩ ዐለፈ። ዐሥራ ሁለቱም ከርሱ ጋራ ነበሩ፤


ኢየሱስ በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል እየሰበከ፣ እንዲሁም ደዌንና ሕመምን ሁሉ እየፈወሰ በከተሞቹና በመንደሮቹ ዞረ።


ከእናንተ ጋራ በነበርንበት ጊዜ፣ “ሊሠራ የማይወድድ አይብላ” ብለን ይህን ትእዛዝ ሰጥተናችሁ ነበርና።


ወንድሞች ሆይ፤ ያለ ሥርዐት ከሚመላለስ እና ከእኛ በተቀበላችሁት ትምህርት መሠረት ከማይኖር ወንድም እንድትርቁ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዝዛችኋለን፤


በጌታ በኢየሱስ ሥልጣን ምን ዐይነት ትእዛዝ እንደ ሰጠናችሁ ታውቃላችሁ።


ለሕዝቡ እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታንም ላይ እንዲፈርድ እግዚአብሔር የሾመው እርሱ መሆኑን እንድንመሰክር እርሱ ራሱ አዘዘን፤


ይኸውም እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ ለመረጣቸው ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የሰጣቸው ትእዛዝ ነው።


የማዝዛችሁን ብትፈጽሙ ወዳጆቼ ናችሁ።


እኔ የአባቴን ትእዛዝ ጠብቄ በፍቅሩ እንደምኖር፣ እናንተም ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።


ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው፤ እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋራ ነኝ።”


ኢየሱስ ማስተማሩን በፈጸመ ጊዜ፣ ሕዝቡ በትምህርቱ ተደነቁ።


ኢየሱስም በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል እየሰበከ፣ በሕዝቡ መካከል ማንኛውንም ደዌና ሕመም እየፈወሰ በመላው ገሊላ ይዘዋወር ነበር።


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ይህን ትእዛዝ ያለ ዕድፍና ያለ ነቀፋ ሆነህ እንድትጠብቅ ነው፤


እነርሱም ከዚያ ወጥተው፤ ሰዎች ንስሓ እንዲገቡ ሰበኩ፤


እነርሱ ግን፣ “ይህ ሰው ከገሊላ ጀምሮ እዚህ ድረስ መላውን ይሁዳ ሳይቀር እያወከ ነው” እያሉ አጽንተው ተናገሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios