ከዚያም በኋላ ዐሥራ አንዱ በማእድ ቀርበው ሲበሉ ኢየሱስ ተገለጠላቸው፤ “ኢየሱስ ከሞት ተነሥቶ በሕይወት አለ፤ በዐይናችንም አይተነዋል፤” ብለው የነገሩአቸውን ባለማመናቸውና በግትርነታቸው ነቀፋቸው።
ማርቆስ 9:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደቀ መዛሙርቱ ግን ይህ ነገር አልገባቸውም፤ እንዳይጠይቁትም ፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ ግን የሚላቸው አልገባቸውም፤ እንዳይጠይቁትም ፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ግን የሚላቸው አልገባቸውም፤ እንዳይጠይቁትም ፈሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ነገሩን አላስተዋሉም፤ እንዳይጠይቁትም ፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ነገሩን አላስተዋሉም፥ እንዳይጠይቁትም ፈሩ። |
ከዚያም በኋላ ዐሥራ አንዱ በማእድ ቀርበው ሲበሉ ኢየሱስ ተገለጠላቸው፤ “ኢየሱስ ከሞት ተነሥቶ በሕይወት አለ፤ በዐይናችንም አይተነዋል፤” ብለው የነገሩአቸውን ባለማመናቸውና በግትርነታቸው ነቀፋቸው።
እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እናንተም ደግሞ ይህን አታስተውሉምን? ከውጪ ወደ ሰው የሚገባ ነገር ሰውን ምንም እንደማያረክሰው አይገባችሁምን?
ኢየሱስ ግን ዘወር ብሎ ደቀ መዛሙርቱን ተመለከተና ጴጥሮስን፦ “አንተ ሰይጣን ከእኔ ኋላ ሂድ! አንተ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን ነገር አታስብም!” ሲል ገሠጸው።
ደቀ መዛሙርቱ ይህ ነገር በመጀመሪያ አልገባቸውም ነበር፤ ግን ኢየሱስ በክብር ወደ ሰማይ ባረገ ጊዜ ይህ ነገር ስለ እርሱ እንደ ተጻፈና ለእርሱም እንደ ተደረገለት አስታወሱ።
ኢየሱስም ሊጠይቁት እንደ ፈለጉ ዐውቆ እንዲህ አላቸው፦ “እርስ በርሳችሁ የምትጠያየቁ፥ ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ደግሞም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዩኛላችሁ’ ስላልኳችሁ ነውን?
በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ከሄዱበት ተመልሰው መጡ፤ ኢየሱስ ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተገረሙ፤ ይሁን እንጂ “ምን ትፈልጋለህ? ወይም ከእርስዋ ጋር ለምን ትነጋገራለህ?” ብሎ የጠየቀው ማንም አልነበረም።